1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋዛ እና ዩክሬይን ጉዳይ የመከሩት የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2016

ዩክሬንና የፍልስጤም ጉዳይ የአዉሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአውሮጳውኑን 2024 አዲስ ዓመት ስራቸውን አሀዱ ብለው የጀመሩባቸው አጀንዳዎች ሆነዋል። ሚኒስትሮቹ ዩክሬንና ሩሲያን ጦርነትና የእስራኤልና ህማስ ጦርነቶችን ትኩረት ሰተው ተወይይተውባቸዋል።

የአዉሮጳ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ
የአዉሮጳ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ ምስል Pond5 Images/IMAGO

የኅብረቱ ሚኒስትሮች የዩክሬንና ሩሲያ ብሎም የእስራኤልና ህማስ ጦርነቶች ትኩረቶቻቸዉ ነበሩ

This browser does not support the audio element.

ዩክሬንና ፍልስጤም፡ የሚኒስትሮቹ ስብሰባ ትኩረት

ዩክሬንና የፍልስጤም ጉዳይ የአዉሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአውሮጳውኑን 2024 አዲስ ዓመት ስራቸውን አሀዱ ብለው የጀመሩባቸው አጀንዳዎች ሆነዋል። የ27ቱ አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት እዚህ ብራስልስ በህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፌ ሚስተር ቦሪየል ስብሳቢነት የዩክሬንና ሩሲያን ጦርነትና የእስራኤልና ህማስ ጦርነቶችን ትኩረት ሰተው ተወይይተውባቸዋል።

የዩክሬን እስራኤልና ፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በየግላቸውና በተናጠል ስለየአገሮቻቸው ሁኒታና የአዉሮጳ ህብረት ተጠባቂ እርዳታና እርምጃ ማብራሪያ እንደሰጡ የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅና የፍልስጠኢም እስስራኤል ችግር፤ ከጆርዳን፤ ግብጽ፤ ሳኡዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና፤ የአረብ ሊግ ዋና ጸሀፊ ጋር የህብረቱ ሚኒስትሮች መምከራቸው ታውቋል።

ዩክሬን አሁንም የህብረቱ ዋና አጀንዳ

የመካከለኛ ምስራቅ ችግር ለዩክሬን የሚሰጠውን ትኩረት እንደማይቀንሰው የገለጹት የውጭ ጉዳይ ኃላፌና የስብሰብው መሪ ጆሴፍ ቦሪየል፤ ወቅቱ የሚስጠው እርዳታ በዓየነትም በመጠንም እንዲጨምር የሚያስገድድ እንጂ የሚቀነስበት ጊዜ እንዳልሆነ  ሚኒስሮቹ እንደተስማሙ አስታውቀውል። “  ግዜው ይልቁንምዩክሬንእራሷን ለመከላከል እንድትችል የበለጠ የገንዘብና የመሳሪያ እርዳታ የሚደረግበት፤ ወታደራዊ ስልጠና ተጠናክሮ የሚሰጥበት ስለመሆኑ ታምኖበታል”፤ በማለት  ዩክሬን አስተማማኝ እርዳታ በምታገኝበት ሁኔታ ላይ እየተሰራ እንደሆነና፤ እንዲዘገይ በተደረገው የ5 ቢዮን ኢሮ እርዳታ ላይም  ክስምምነት እንደሚደረስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የእስራኤልና ፍልስጤም ሚኒስትሮች ለስብሰባው ያቀረቡት ጥሪ  

በመካከለኛው ምስራቅ አጀንዳ ላይ ግን የእስራኤልን ጨምሮ የፍልጽጤምና ሌሎች ያረብ አገሮች ሚኒስትሮች በአስረጅነት የተሳተፉበትና ክርክሮችም የተካሄድበት እንደነበር ነው የተገለጸው። የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር  ሚስተር እስራኤል ካትዝ ወደ ስብሰባው ከመግባታቸው በፊት ለጋጤጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ አገራቸው የምታካሂደው ጦርነት የታገቱ ዜጎቿን ለማስለቀቅና ያገሯን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ እንደሆነና ይህንኑ ለሚኒስትሮቹ ስብሰባ ለመግለጽ እንደመጡ  አስታውቀዋል።

የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ሚስተር ሪያድ አል ማሊኪ በበኩላቸው ባለፉት ሶስትና ተኩል ወራት በየቀኑ የቆስሉ የሚገደሉና ከፍርስራሾች የሚወጡ ፍልስጤሞች ቁጥር በብዙ ሺዎች የሚቆጠር መሆኑን በመግለጽ፤ ወደ ስብሰባው የመጡበትን ምክኒያት ግልጽ አድርገዋል፤ “ እዚህ ዛሬ የመጣሁት ከሁሉም በፊት ሊደረግ የሚገባው የተኩስ ማቆም መሆኑን ለማሳሰብ ነው። ሁላችንም የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደርግ መጭህ አለብን”፤ በማለት ይህን ለመጠየቅ መዘግየት፤ በሺ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ ሴቶችና አረጋውያን ግድያ እንዲቀጥል መፍቀድ ነው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ ላይ የቀረበ ትችት

የስብሰባው መሪ ሚስተር ቦርየልም እንደዚሁ ከስብሰባው በፊት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን  ናታኒያሁ የሁለት መንግስታትን የመፍሄ ሀሳብ አልቀበልም ማለታቸውን በሚመለክት ለቀረበላቸው ጥያቄ ፤ “ የበለጠ ግድያ፤ ጥፋትና የጋዛን ህዝብ ለባሰ ችግር መዳረግ፤ ሃማስንና አስተሳሰቡን የሚያሸንፍ ወይም የሚያጠፋ አይደለም፤ ለስራኤልም የደህንነት ዋስትና አያመጣም” በማለት ከዚህ አዙሪት ለመውጣት፤ አለማቀፍ አጋሮች ሁሉ በጋራ  በሁለት መንግስታት የመፍትሄ ሀሳብ ላይ  መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአዉሮጳ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ ምስል picture alliance /

የማጠቃለያ ሀሳቦችና የተሰጡ አስተያየቶች  

ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው ማጠቃለያ፤ የሚገደሉ ሰላማዊ ፍልስጤሞች ቁጥር እየጭመረ መሄዱ፤ በጋዛ የተንሰራፋው እርሀብና የእርዳታ በበቂ ሁኒታ አለመድረስ፤ እንዲሁም የታገቱ እስራኤላውያን ጉዳይ  አስቸኳይ መፍትሄ የሚሹ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ የጦርነትና የእልቂት አዙሪት ለመውጣት ለችግሩ ዘላቂ መፍሄ መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን ያመኑት የኅብረቱ ሚኒስትሮች፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቢያም ናታኒያሁ የሁለት መንግስታት የመፍትሄ ሀሳብን አልቀበልም ማለታቸውን እንዳወገዙም ተገልጿል። ከዚህ ውጭ ግን የህብረቱ ሚኒስትሮች ዛሬም በአንድና ሙሉ ድምጽ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ እንዳላቀረቡ ነው የታወቀው። በእርግጥ የወቅቱ የህብረቱን ፕሬዝደንሲ የያዘችው ቤልጀየም፣ ስፔንና አየርላንድ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲደረግ ሲገፉ የነበር መሆኑ ቢታወቅም ይህ ግን ቢያንስ ለግዜው   የሁሉም ድምጽ ሆኖ  አልተሰማም። ከአንድ ሳምንት በኋላ ግን በዋናነት  በእነዚሁ ሁለት አጀንዳዎች ላይ የሚመክር ልዩ  የ27ቱ አባል አገሮች መሪዎች ጉባኤ እዚህ ብራስልስ እንደሚካሄድ ታውቋል።

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW