1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዋሳ ከተማ አስተዳደር እርምጃና የነዋሪው ተቃውሞ

ዓርብ፣ የካቲት 11 2003

የአዋሳ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ የአርሶ አደር መሬት ገዝተው መኖሪ ቤትና የተለያዩ ግንባታዎችን ያከናወኑ ናቸው ባላቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ገልጿል።

ከ1985 ጀምሮ በተለይ ዳቶ በተሰኘው አከባቢ መኖሪያ ቤት ሰርተው እየኖሩ እንደሆኑ የሚገልጹት ነዋሪዎች መንግስት ያለምንም አማራጭ ሊያፈናቅለን ነው ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። የከተማው ማዘጋጃ ቤት ምን ዓይነት እርምጃ እንደሚወሰድ ከራሱ ከነዋሪው ጋር በመነጋገር የሚወሰን ነው በማለት ገልጿል። ይህን በመጠየቃችን ሰዎች እየታሰሩ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ ግን ህዝብን መንግስት ላይ ለማሳመጽ የሞከሩትን እንጂ አንድም ሰላማዊ ሰው አላሰርንም ይላሉ። ወደ አዋሳ ስልክ በመደወል ቅሬታ አቅራቢዎቹንና የከተማዋን ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ አነጋግሬአለሁ።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW