1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

የአዋሽ እና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 8 2013

በአዋሽ እና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎችን ባካተተው የጋራ ፎረም የሀረማያ ፣ የድሬደዋ ፣ የጅግጅጋ ፣ ቀብሪዳሀር ፣ ኦዳ ቡልቱም ፣ መደ ወላቡ ፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፣ አምቦ ፣ ወሎ እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎችን ያካተተ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎቹ የተቀናጀ እና የተናበበ ምርምር ማድረግ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

Äthiopien Wabi Shebele Basin Universitätsforum
ምስል Messay Teklu/DW

የአዋሽ እና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም መሰረቱ

This browser does not support the audio element.

በአዋሽ እና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም ተመሰረተ ፡፡ ፎረሙ የተቀናጀ እና የተናበበ ምርምር ማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የአዋሽ እና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ምስረታ ላይ የተገኙት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን ለዘላቂ ልማት እና ተፈላጊ ውጤት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

ልማትን ወደ ሀገሪቱ ለማምጣት ከተለዩ አምስት ዘርፎች አንዱ እና ቀዳሚው ግብርና መሆኑን የጠቀሱት ሚንስተር ዲዔታው በግብርናው ዘርፍ የተቀጠውን ግብ ለማሳካት ፎረሙ የተለየ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በፎረሙ የተካተቱ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ስራውን በተለየ መንገድ እንዲመሩት ጠይቀዋል፡፡

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ በበኩላቸው ግብርና ለሰፊው ህዝብ በተለይ ለወጣቶች ሳቢ ዘርፍ ላለመሆኑ የተማረው ሀይል በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሓላፊነት መወሰድ አለባቸው ብለዋል ምክንያቱም እርሻ ለወጣቱ ሳቢና ተመራጭ ለመንግስትም በዕቀውቀት የተደገፈ የፖሊሲ አማራጭ ማቅርብ የተቋማቱ ሚና ስለሆነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይህ ማለት ዩኒቨርሲቲዎቹ ምንም ስራ አልሰሩም ማለት አለመሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ  እንደ አንድ እርምጃ የፎረሙ መመስረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዘርፉ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል፡፡

በአዋሽ እና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎችን ባካተተው የጋራ ፎረም የሀረማያ ፣ የድሬደዋ ፣ የጅግጅጋ ፣ ቀብሪዳሀር ፣ ኦዳ ቡልቱም ፣ መደ ወላቡ ፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፣ አምቦ ፣ ወሎ እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎችን ያካተተ መሆኑ ታውቋል ፡፡

በፎረሙ ምስረታ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር እና የየዩኒቨርሲቲው አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ምሁራን እና እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW