1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአዋሽ ወንዝ ሙላት ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 30 2012

በመታሓራ ከተማ በደራሽ ውሃ ከተጥለቀለቁት ሃሮ አዲ እና በተለምዶ ጨረቃ ሰፈር ተብሎ ከሚጠሩ አከባቢዎች ተፈናቅለው አሁን ላይ በመሃል የመታሃራ ከተማ ተጠልለው ያሉት ቁጥራቸው ከ30 ሺህ እንደምልቅ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት አካላት መረጃ ደግሞ እስካሁን የተፈናቃዮች ቁጥር 19 ሺህ ገደማ መሆኑን አረጋግጠውልናል፡፡

Äthiopien | Überschwemmungen des Fluss Awash
ምስል፦ DW/S. Getu

በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር እያሻቀበ ነው

This browser does not support the audio element.

ሰሞኑን በአዋሽ ወንዝ እና የበሰቃ ሃይቅ ሙላትን ተከትሎ በመታሃራ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያሻቸው ተነገረ፡፡

 አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት እስካሁን በቂ የሆነ የመጀመሪያ ደረጃ የድጋፍ ቁሳቁሶች ከመንግስትም ሆነ ሌሎች ድጋፍ ሰጭ ተቋማት ያልደረሰ በመሆኑ ድጋፉ ከከተማዋ ነዋሪዎች ርብርብ በላይ እየሆነ መጥቷል ፡፡

በመታሓራ ከተማ በደራሽ ውሃ ከተጥለቀለቁት ሃሮ አዲ እና በተለምዶ ጨረቃ ሰፈር ተብሎ ከሚጠሩ አከባቢዎች ተፈናቅለው አሁን ላይ በመሃል የመታሃራ ከተማ ተጠልለው ያሉት ቁጥራቸው ከ30 ሺህ እንደምልቅ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት አካላት መረጃ ደግሞ እስካሁን በምዝገባ የተለየው የተፈናቃዮች ቁጥር 19 ሺህ ገደማ መሆኑን አረጋግጠውልናል፡፡

በደራሽ ውሃው የበርካታ ዜጎች ንብረት ከአገልግሎት ውጭ መሆኑን የሚያስረዳው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ እስካሁን ህይወት የመታደግ ስራ ላይ ማተኮሩን በመግለጽ፤ ከአሁን በኋላ ደግሞ ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ የማድረግ ስራ ቅድሚያ ያገኛል ብሏል፡፡

የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳውድ ሙሜ ለዶይቼ ቨለ እንደተናገሩት 1.2 ሚሊየን ብር የሚገመት የአልባሳትና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ በስፍራው ደርሷል ብለዋል፡፡ በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ የውሃ ሙላቱ መፈናቀልን ያስከተለው በከተማ ነዋሪዎችና በአርብቶ አደር ማህበረሰብ ላይ በመሆኑ የሰው ህይወትን ከመታደግ ጎን ለጎን የአርብቶ አደሩ ሃብት ንበረትም የመዳን ስራ ትኩረት ማግኘቱን አቶ ዳውድ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ውሃው ቀንሶ ነዋሪዎቹን ወደ መኖሪያ ቀዬያቸው ለመመለስ ዘለግ ያለ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል ሰብዓዊ ድጋፉ ቀጣይነት እንዲኖረው ከተለያዩ ድጋፍ ሰጭ ተቋማት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች ሰፊ ቦታዎችን የሚሸፍነው የአዋሽ ተፋሰስን ተከትሎ የሚደርሱ የውሃ መጥለቅለቅ ስጋቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ባለሙያ እና ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ውይይት እየተደረገ ስለመሆኑም ዶይቼ ቬለ ከምንጮች ተረድቷል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW