1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት ተቋማት የ2024-2029 መሪዎች

ዓርብ፣ ሰኔ 21 2016

የአውሮጳ ህብረትን የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ስታራቴጂክ አጀንዳዎች ለማጽደቅና የህብረቱን ተቋማት የሚመሩ ባለስልጣናትን ለመስየምና ለመምረጥ ለሁለት ቀናት የተጠራው የ27ቱ የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ፤ መሪዎቹን መርጦ፤ በአጀንዳዎቹ ላይ ተወያይቶና ወስኖ ከተያዘው ፕሮግራም ቀደም ብሎ ትናንት ዕከለ ሌሊት ላይ ተጠናቋል።

የ27ቱ የአዉሮጳ ሃገራት የመሪዎች ጉባዔ
የ27ቱ የአዉሮጳ ሃገራት የመሪዎች ጉባዔምስል Geert Vanden Wijngaert/AP/picture alliance

የአውሮጳ ህብረት ተቋማት የ2024-2029 መሪዎች

This browser does not support the audio element.

የአውሮጳ ህብረት ተቋማት የ2024-2029 መሪዎች

የአውሮጳ ህብረትን የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ስታራቴጂክ አጀንዳዎች ለማጽደቅና  የህብረቱን ተቋማት የሚመሩ ባለስልጣናትን ለመስየምና ለመምረጥ ለሁለት ቀናት የተጠራው የ27ቱ የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ፤ መሪዎቹን መርጦ፤በአጀንዳዎቹ ላይ ተወያይቶና ወስኖ ከተያዘው ፕሮግራም ቀደም ብሎ ትናንት ዕከለ ሌሊት ላይ ተጠናቋል። የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ሚስተር ሚሸል ዕኩለ ሌሊት ላይ ወተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤  ጉባኤው ተልኮውን አሳክቶ ያበቃ መሆኑን በመግለጽ የህብረቱን ተቋማት ለቀጣይ አምስት አመታት እንዲመሩ የተሰየሙትን ስም ዝርዝር ይፋ አድርገዋል፤ “ ተሳክቷል፤  የአዉሮጳ ህብረት ወስኗል፤. ዛሬ ልንወስንባቸው የሚገባ ወሳኝ አጀንዳዎች ነበሩ፤ እነሱንም አሳክተናል›። የተወሰኑትን ውሳኔውችን የተመረጡትን መሪዎች የምገልጽላችሁ በታላቅ ክብርና ደስታ ነው” በማለት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴር ሌየን ለቀጣይ አምስት አመታት የኮሚሽኑ ፕሬዝዳደንት ሁነው እንዲቀጥሉ፣ ቀድሞ የፖርቱጋል፤ ጥቅላይ ሚኒስተር፤ ሚስተር አንቶኒዮ ኮስታ፤ ሚስተር ቻርለስ ሚሸልን በመተካት የክውንስሉ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ፤ የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ካያ ካላስ  ደግሞ ሚስተር ጅጆፍ  ቦርየልን ተክተው የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሆነው እንዲሰሩ የተመረጡና የተሰየሙ መሆኑን አስታውቀዋል።

የተሿሚዎች አስተያየት

ወይዘሮ  ፎንደር ሌየንም " ለሁለተኛ ግዜ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እንድሆን  የመረጡኝን  የህብረቱን መሪዎች ከልብ አመሰግናለሁ” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል። ሚስተር ኮስታ፤ “የተሰጠኝን ሹመት የምቀበለው በታላቅ ሀላፊነት ነው” በማለት  የህብረቱን አባል አገራት አንድነት ተጠብቆና ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚሰሩ መሆኑን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልክት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር ካያ ካላስ ደግሞ መሪዎቹ ባሳዩዋቸው ድጋፍና ምርጫ ክብር የሚሰማቸው መሆኑን ገልጸው፤ ሀላፊነቱ በተለይ በአሁኑ  የጂኦፖልቲክዊ ውጥረት ባለበት ወቅት ከፍተኛ መሆኑን እንደሚረዱና በዚህ ውስጥ የአዉሮጳን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የ27ቱ የአዉሮጳ ሃገራት የመሪዎች ጉባዔምስል Olivier Hoslet/AP/picture alliance

የተሿሚዎቹ ምርጫ አስቸጋሪነት እንዴትነት

የሦስቱ ባለስልጣኖች ሹመት ተጠብቆ የነበር ቢሆንም አስጨናቂ ግን እንደነበር ነው ጉዳዩን የተክታተሉ የሚናገሩት። ከሁለት ሳምንታት በፊት የተካሄደው የአዉሮጳ ፓርላማ ምርጫ ነባሮቹን በተለይም  የየመሀል ግራዎቹን፣ የሊበራሎቹንና አረንጓዴዎሹን ፓርቲዎችን ያንገዳገደና ባንጻሩ በበአዉሮጳ ህብረት አካሄድ ላይ ጥያቄ ያላቸውንና በተለምዶ ኢሮሲኬፕቲክ የሚባሉትን የቀኝ ፓርቲዎችን ወደፊት ያመጣ በመሆኑ የተቋማት መሪዎች ያመራረጥ ሂደት እንደከዚህ ቀደሙ ቀላል አልሆነም።

የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ስለ ህብረብቱ የወደፊት አሰራርና የተቋማቱ መሪዎች አመራርጥ ላይ ለመወያየት  ካስር ቀናት በፊት በተጠራ መደበኛ ያልሆነ የመሪዎች ስብሰባ ከስምምነት መድረስ ያልተቻለ እንደንበር የሚይታወስ ሲሆን፤ ክዚያ በሁላ  የነባሮቹ ፓርቲዎች መሪዎችና ሀላፊዎች በተለይም የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሹልስ፣ የኒዘርልድስ፤ የፖላንድና የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በግል መክረውና ዘክረው ያቀረቡት የስም ዝርዝር  እንደጽደቀ ነው የተገለጸው። ይህ አሰራር ግን የምርጫውን ውጤት ያላገናዘበና ዴሞክራሲያዊ ያልህነ ነው በማለት ከጣሊያንና ከሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተቃውሞ ገጥሞት ስልነበር ነው አንዱ የምርጫውን ሂደትና ውጤት ተጠባቂ አድርጎት የቆየው።

የተሿሚዎቹ ሹመት መጽደቅ ሂደት

የወይዘሮ ፎንዴርልየን ሹመት እንደገና ከሁለት ሳምንታት  በሁላ በሚካሄደው ያውሮፓ ፓርላማ ስብሰባ ድምጽ የሚሰጥበት ሲሆን፤ ከ720ዎቹ የፓርላማ አባላት ቢያንስ የ361 አባላቱን  አብልጫ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። አንዳንድ እንደራሴዎች ከፓርቲዎቻቸው መስመር ውጭ ድምጽ ሊሰጡ ስለሚችሉ ወይዘሮ ቮንዴርልየን የሌሎቹን ቡድኖች አባላት ድምስ ለማግኘት ተጨማሪ ስራ ይጠብቃቸዋል እየተባለ ነው።ጠቅላይ ሚኒስተር ካላስ ግን በፓርላማው ቀርበው ስለእየቅዳቸው መግለጫና ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ክመስጠት ውጭ ሹመታቸው ድምጽ ሚሰጥበት አይሆንም። ሚስተር ኮስታም ወደ ፓርልማው መሄድ ሳይስፈልጋቸው በቀጥታ ከመጨው  ታህሳስ ወር መጀምሪያ ጀምሮ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ነው ሚታወቀው።

የ27ቱ የአዉሮጳ ሃገራት የመሪዎች ጉባዔምስል Olivier Hoslet/AP/picture alliance

ጉባኤው በሌሎች  አጀንዳዎች ላይ

የመሪዎቹ ጉባኤ ከአምስት ዓመቱ የህብረቱ ስታራቴጂክ እቅድና የተቋማት ሹመት በተጨማሪ በዩክሬንና፣ መካከለኝው ምስራቅ አጀንዳዎች ተወይይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ሚስተር ዜለንስኪም በጉባኤው የተገኙ ሲሆን፤ ከህብረቱና ሌሎች የህብረቱ አባል አገራት  ጋርም የሁለትዮሺ የጋራ ደህንነት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። ከህብረቱ ጋርም ይሁን ካአባል አገራቱ ጋር የተፈራረሟቸው ውሎች ግን  የጋራ ደህንነት ውሎች እንጂ ወታደራዊ ስምምነቶች አይደሉም ተብሏል።

በመከከላኛው ምስራቅ ላይ  ጉባኤው  የምንግስታቱ ድርጅት ያሳለፈው የተኩስ ማቆም ጥሪ ተቀባይነት እንዲያገኝና የሰባዊ እርዳታ ያለምንም መሰናክል እንዲገባና ለዘላቂ ሰላምም የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ መድረስ  ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ጥሪ ያቀረበ መሆኑም  ተገልጿል።

ገበያዉ ንጉሴ 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW