1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሀገራት እና ስደተኞችን የማከፋፈሉ ጉዳይ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 14 2007

የአውሮጳ ህብረት የሀገር አስተዳደር ሚንስትሮች ትናንት በብራስልስ ቤልጅየም ባካሄዱት ስብሰባ በኢጣልያ እና በግሪክ ከሚገኙት 40,000 ስደተኞች መካከል ቢያንስ 32,000 በተለያዩ የህብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ እንዲሰፍሩ መስማማታቸው ተገለጸ።

Symbolbild Flüchtlinge Mittelmeer EU
ምስል Reuters/I. Zitouny

[No title]

This browser does not support the audio element.

የተቀሩትን 8,000 ደግሞ የፊታችን ታህሳስ እንደሚያሰፍሩ ሚንስትሮቹ አስታውቀዋል። ስደተኞቹን በአባል ሀገራቱ መካከል በኮታ ለማከፋፈል በተደረገው ጥረት ላይ በአባል ሀገራት መካከል ልዩነት ከተፈጠረ በኋላ፣ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች ሀገራት በፍላጎት የሚችሉትን ያህል እንዲቀበሉ ባለፈው ሰኔ ወር ቢስማሙም፣ ምን ያህሉን በሚለው ቁጥር ላይ ስምምነት የደረሱት ግን ገና በትናንቱ ስብሰባቸው ላይ ነበር።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW