የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት
ረቡዕ፣ ግንቦት 8 2010ማስታወቂያ
የአውሮጳ ህብረት፣የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውድቅ ያደረገቱን የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ፈረንሳይ ብሪታንያ ጀርመን የአውሮጳ ህብረት ሩስያ እና ቻይና ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የጣለችው ኢራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን የሚያግደው ስምምነት ፈራሚ ናቸው። ከሳውዲ አረብያ እና ከእሥራኤል በስተቀር የአሜሪካ ወዳጅ እና አጋር የሚባሉትን የአውሮጳ ሀገሮችን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአሜሪካንን እርምጃ አውግዘዋል። የኢራን የኒዩክልየር ስምምነት ፈራሚዎች ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ መክረዋል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ