የአውሮጳ ህብረት ካውንስል ፕሬዚዳንት የቻይና ጉዞ
ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2015ማስታወቂያ
ቻይና በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ከህብረቱ ጋር ንግግር ለመቀጠል መስማማቱን በበጎ ጎኑ እንደሚቀበል የአውሮጳ ህብረት አስታወቀ። የህብረቱ ካውንስል ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሸል ወደ ቻይና ተጉዘው ከፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቻይና ከህብረቱ ጋር በንግድ ፣ በዓለማቀፍ ሰላም እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ለመነጋገር ብሎም አብሮ ለመስራት ፍላጎት አሳይታለች። የአውሮጳ ሕብረት እና የቻይና የጋራ ጉባኤ የህብረቱ ካውንስል ፕሬዚዳንት በተጨማሪ በታይዋን ፣ የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ተነጋግረዋል። የካውንስሉ ፕሬዚዳንት የቻይና ጉዞ አንድምታ በመለከተ የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግረነዋል።
ታምራት ዲንሳ
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ