የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 9 2011
ማስታወቂያ
ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም የተሰበሰቡት የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከኢራን ጋር በተደረገው የኒውክለር ስምምነት ቀጣይነት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። በውይይቱ አጀንዳ ውስጥ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እና ሱዳንም ተካተው ነበር። ከስብሰባው በኋላ የህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ፌደሪካ ሞጎሮኒ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። መግለጫውን የተከታተለው የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ