የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ውሳኔና ኢትዮጵያ
እሑድ፣ ጥር 15 2008ማስታወቂያ
የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ሰሞኑን ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ በመካሄድ ላይ ባለው መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ፓርላማው ትናንት ባሳለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ይፈፅማል የሚባሉትን የመብት ጥሰቶች ተቃውሟል። በሃገሪቱ በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት በጋዜጠኞችና አምደኞች ላይ የሚደርስውን ውንጀላ ፍረጃ እስራትና ቁም ስቅልም ከፍተኛ የመብት ጥሰት ብሎታል። ከአዲስ አበባና ኦሮምያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በተለይ በኦሮምያ አካባቢዎች ጥያቄ ባነሱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተወሰደውን የኃይል እርምጃም አውግዟል።ፓርላማው በዚሁ ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህን መሰሉ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠብ አሳስቦ ካለፈው ሰሞን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጋርም ሆነ ከዚያ በፊት የታሰሩትን ተማሪዎች ገበሬዎች ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈታ እንደራሴዎቹ ባሳለፉት ውሳኔ ጠይቀዋል። የብራሰልሱ ወኪላችን ፓርላማው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያሳለፋቸውን ሌሎች ውሳኔዎችና በውሳኔው ላይ የተሰጠ አስተያየት ያካተተ ዘገባ አዘጋጅቷል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ