የአውሮጳ ሕብረትና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባዔ በማልታ
ረቡዕ፣ ኅዳር 1 2008ማስታወቂያ
የአውሮጳ ኮሚሽን ከአፍሪቃ የሚመጡትን ስደተኞች ለመግታትና ለስደት የሚያበቁ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል 1.8 ቢሊዮን ዩሮ መመደቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ ጉባዔው በእቅዱና አፈጻጸሙ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ፣ የልማት ርዳታውም ሆነ የተነደፈው ስልት፣ የችግሩን መሰረት የሚነካ አይደለም እየተባለ ነው። በተጨማሪም ስደተኖቹ በአውሮጳ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ህይወት ላይ ያሳደሩት ጫና ተጋኖዋል የሚል ክርክርም ይሰማል። የዛሬው ከኢኮኖሚው ዓለም ዝግጅት፣ የቫሌታውን ጉባኤ ሂደትና ውጤት እንዲሁም ስደተኖች በተለይ በአውሮጳ ኢኮኖሚ ላይ የሚያስድሩትን ተጽኖ ይመረምራል።
ገበያዉ ንጉሴ
አርያም ተክሌ