1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ምርጫ

ረቡዕ፣ ሰኔ 26 2011

የአውሮጳ ሕብረት መሪዎች ከተራዘመ የስብሰባ እና የድርድር  ጊዜ በኋላ  የሕብረቱን ተቋማት ይምሩን ያሏቸውን ባለሥልጣናት መረጡ። ዛሬም የሕብረቱ ፓርላማ ፕሬዝደንት በአብላጫ ድምፅ ተመርጠዋል።

Neuer Präsident des EU-Parlaments David Sassoli
ምስል picture-alliance/AP Photo/J.-F. Badias

ዴቪድ ማሪያ ሳሶሊኒ የሕብረቱ ፓርላማ ፕሬዝደንት ሆኑ

This browser does not support the audio element.

 ለሕብረቱ ፓርላማ ሊቀመንበርነት የጣሊያኑ የምክር ቤቱ አባል ሶሻል ዴሞክራቱ ዴቪድ ማሪያ ሳሶሊኒ 345 ድምፅ  አግኝተው የተመረጡ ሲሆን፤ ፈረንሳዊቱ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ክርስቲን ላጋርድ ደግሞ የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ  ፕሬዝደንት ሆነዋል። የሕብረቱ መሪዎች በተለመደው መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕብረቱን ትላልቅ  የኃላፊነት ቦታዎች  የሚይዙ ባለሥልጣናትን  በመምረጡ  ከመግባባት ከመግባባት ለመድረስ ጊዜ ፈጅተዋል።  ለዚህም አንድም ባለፈው ግንቦት የተካሄደው ምርጫ ያስከተለው ያልተጠበቀ  ውጤት፤ አንድም ሃገራት በተናጠልም ሆነ በአካባቢ ይገባናል የሚሉትን ጥቅም ለማስጠበቅ የነበረው ፉክክር በምክንያትነት ይጠቀሳል። ገበያው ንጉሤ ከብራስልስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW