1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረት በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ

ዓርብ፣ ሰኔ 2 2015

የ27ቱ የአውሮፓ ህብረት የአገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትሮች ለሁለት ቀናት በሉክዘምበርግ ከተማ ባካሂዱት ስብሰብ በአዋዛጋቢው የስደተኖችና ፈላሲያን አጀንዳ ላይ ተስማምተው የጋራ የስደተኞች ውል አጽድቀዋል። ወደ ሕብረቱ የሚገቡ ስደተኞችና ፈላስያን ቁጥር በየግዜው በከፍተኛ ደረጃ እይጨምረ መሄዱም በዚሁ ጊዜ ተገጿል።

Luxembourg EU-Minister Migrationsabkommen
ምስል RTRTV

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በስደተኞች ጉዳይ ከስምምነት ደረሱ

This browser does not support the audio element.

የ27ቱ የአውሮፓ ህብረት  የአገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትሮች ለሁለት ቀናት በሉክዘምበርግ ከተማ ባካሂዱት ስብሰብ በአዋዛጋቢው  የስደተኖችና ፈላሲይን አጀንዳ ላይ ተስማምተው የጋራ የስደተኖች ውል ያጸደቁ መሆኑ ተገልጿል። ወደ ህብረቱ የሚገቡ ስደተኖችና ፈላስያን ቁጥር በየግዜው በክፍተኛ ደረጃ እይጨምረ መሄዱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም በጣሊያንና ግሪክ በመሳሰሉት የህብረቱ የስደተኖች መዳረሻ አገሮችና በሌሎቹ መካከል ልዩነቶች ተፈጥረው ቆይተዋል። መዳረሻዎቹ አገሮች በነሱ በኩል የሚገቡት ስደተኞች ጉዳይ የሁሉም የህብረቱ አገሮች ጉዳይ መሆን አለበት በማለት ሁሉም በዚህ በኩል ያለባቸው ሀላፊነት እንዲወጡ ሲጠይቁና ሲያሳስቡ ቆይተዋል ። የአውሮፓ ኮሚሽንም በተለይ እ እ እ በ2015 ም ከተከሰው የስደተኞች ቀውስ ወዲህ፤ አባል አገራቱ በግልና በጋራ ሀላፊነተታቸውንና ግዴታቸውን የሚወጡበት አንድ የጋራ አስገዳጅ የስደተኞች ውል ወይም ህግ እንዲኖር ሲሰራ የቆየ ሲሆን፤ ዛሬ ባበቃው የሉክዘምበርጉ ሚኒስትሮች ስብሰባ የጸደቀውም ይህ ኮሚሽኑ ለአመታትት ሲገፋው የነበረው ውል ነው ።

 ከህብረቱ አገሮች የተለያዩ ፍላጎትች  አንጻር ይህ የጋራ ፖሊስ ወይም ውል ተቀባየነት የማግኘቱ ሁኒታ አጠራጣሪና አስጨናቂም የነበረ መሆኑን የወቅቱ የህብረቱ ፕሬዝዳንሲና የስብሰባው መሪ የስዊደን የፈላስያንና ስደተኖች ሚኒስተር ወይዘሮ ማሪያ ማልሜር ስቲኔርጋርድ  አልሸሸጉም፤ “ እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ ይህን የመሰለ ወሳኔ ይዠ እቀርባለሁ ብየ አላሰብኩም።  ሚኒስትሮቹ  በፈላስያንና ስደተኖች አስተዳደርና በስደተኖች የአቀባበል ስራት ህጎች ላይ የቀረበውን የጋራ ውል አጽድቀዋል” በማለት ይህም ትልቅ ስኬት መሆኑን አብስረዋል።

ወይዘሮ ማሪያ፤ ስምምምነት የተደርሰባቸው ሁለቱ ፋይሎች የህብረቱ የስደተኖች ፖሊስ ማሻሻያ ምሰሶዎች መህናቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል። “ሁለቱ የጸደቁት ሰነዶች ሀላፊነትንና ግዴታን ያጣመሩ፣ የአውሮፓን እሴቶች መሰረት አድርገው የስደተኖችንና ፈላሲያንን ጥያቄ ለማስተናገድና ለማስተዳደር የሚረዱ የጋራ ፖሊሰው ማዕከል ናቸው” በማለት ውሳኔው ታሪካዊ መሆኑን ገልጸዋል

የስደተኞች አቀባበል ስራት ህግ፤ ሁሉም የህብረቱ አገሮች ወጥ የሆነ ሂደትና አሰራር  እንዲከተሉ የሚጠይቅ ሲሆን፤ የስደተኖችና ፈላስያን አስተዳደር ህግ  ደግሞ ቀድሞ የንበረውን የደብሊን ህግ የሚተካና ስድተኖች የት ተገን መጠየቅ እንደሚችሉ የሚገልጽ ነው።

 በዚህም መሰረት ሚኒስትሮቹ የተስማሙበትና ያጸደቁት የጋራ የስደተኞች ውል፤ ሁሉ የሀበረቱ አገሮች ወደ ህብረቱ ለገቡ ስደተኖችና ፈላስያን ሀላፊነት እንዳለባቸውና ስደተኖችን በኮታ የመውሰድ  ወይም በገንዘብ የመደገፍ ሀላፊነት እንዳለብቸው ይደነግጋል። ስደተኖች ጥያቄያቸው በመጀመሪያ በሚገቡባቸው አገሮች ምላሺ እንዲያገኝ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ጥያቄአቸው ውድቅ የሆኑባቸውን  አገሮቹ፤ ወደሌላ ሶስተኛ አገር እንዲሉኳቸው መብት ይሰጣል። ስደተኖቹ ተመልሰው በሚላኩባቸው አገሮች የደህንነት ዋስታ የሚያገኙ ስለመሆናቸው ግልጽ አለመሆኑ ግን  በብዙዎች የመብት ተሙጋቾች የሚነሳ ጥያቄ ሁኗል ።  

ስምምነቱ የጸደው በድምጽ ብልጫ ሲሆን ጣሊያን ዋናዋ የስደተኖች መግቢያ በር በመሆኗ ይሁንታዋ ወሳኝ ነበር ነው የተባለው።

ሚስትሮቹ በተጨማሪም፤ በሸንገን ቪዛ፣ የሰው አዘዋዋሪ ወንጀል መከላከልና በፕሬስ ነጻነት አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል ። በጦርነቱ ምክኒያት ከዩክሬን ሊሚመጡ ስደተኖች እየተደረገ ስላለው ድጋፍና የተሰጠው ግዚያዊ የመቆያ ፈቃድ እንዴት መራዘም እንዳለበት፤  በሚቀጥለው ስብሰባ የሚመክር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ግን ከሌሎች አካባቢዎች እንደዚሁ በጦርነት ተፈናቅለውና ተስደው አውርፓ ለደረሱ ስደተኖች አውሮፓ ፊቱን ማዞሩ ሲያንስ  አድሏዊነት ሲበዛ ዘረኝነት ነው በማለት የመብት ተሟጎችች ጩኸት ማሰማት ይዘዋል ።

ዛሬ ስምምነት የተደረበት የህብረቱ የስደተኖች ማሻሻያ  ውል ባውሮፓ ፓርላማ መጽደቅ የሚኖርበት ሲሆን፤ ይህም ከአመቱ መጨረሻ በፊት እንደሚሆን  ይጠበቃል።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW