1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ

ማክሰኞ፣ ጥር 16 2015

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰፊውን ግዜ ከወስደው የዩክሬን አጀንዳ ውጭ በፍልስጤም፣ አፍጋኒስታን፤ አርሜኒያ’ የሳህል አገሮች፣ ኢራንና ኢትዮጵያም ጭምር መወያየታቸው ታውቋል። በኢራን በተቃዋማዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚወሰደውን የሀይል እርምጃና ግድያ ሚኒስትሮች አጥብቀው ያወገዙ መሆኑን ሚስተር ቦርየል በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት አስታወዋል።

Belgien | EU Flaggen in Brüssel
ምስል Kenzo Tribouillard/AFP/Getty Images

የአውሮፓ ሕብረት አባል ሃገራትየውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ

This browser does not support the audio element.

ባለፈው የአውሮጳውያኑ ዓመት የአውሮፓ ህብረት አይነተኛና አሳሳቢ አጀንዳ ሆኖ የቆየው የዩክሬን ጦርነት በአዲሱ ዓመትም ይበልጥ አሳስቢና አስጊ በመሆን ጭምር አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው። ትናንት እዚህ ብራስል የተካሄደው የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የዓመቱ የመጀመሪያ ስብሰባም በዋናነት የተወያየውና ውሳኔዎችን ያሳለፈው  በዚሁ ሩሲይ በሩክሬን ላይ በከፈተችው  ጦርነት ላይ ነው።፡ 
የህብረቱ የውጭ ጉድይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል በጋዜጣዊ መግለጫቸው የዓመቱን የመጀመሪያ ስብሰባችንን በዩክሬን መጀመር ነበረብን ምክኒያቱም ሩሲያ በዩክሬን ከተሞችና ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየፈጸመች ያለው ጫክኔ የተሞላበት ጥቃት የቀጠለ በመሆኑ ነው’  በማለት ህብረቱ ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ እንደሚቀጥልና ዩክሬንም ጦርነቱን ከማሸነፍ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላልት አስታውቀዋል።  
ሚኒስትሮቹ ተጨምሪ  500 ሚሊዮን ኢሮ ወታደራዊ እርዳታ ለመስጠት የተስማሙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ45 ሚሊዮኑ ህብረቱ የዩክሬን ወታደሮችን ለማሰልጠን ለያዘው ዕቅድ እንደሚውል ተገልጿል።  ጦርነቱ ባለፈው የካቲት ወር መጨርሻ ከተጅመረ ወዲህ ህብረቱ ለዩክሬን 50 ቢሊዮን ኢሮ የሚጠጋ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሀላፊው አክለው ገልጸዋል። 
ለዩክሬን ከሚስጠው ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ እርዳታ ጎን ለጎን ህብረቱ በሩሲያ ላይ ልዩ ልዩ እርምጃዎችን እየወስደ መሆኑንም ሚስተር ቦርየል አውስተዋል። የፕሬዝዳናት ፑቲን መንግስትና ባለስልጣኖቻቸው በዩክሬን እየፈጸሙት ላለው ጥቃትና ወንጀል ተጠያቂ በሚሆኑበት ላይም ህብረቱ እየሰራ እንደሆነ በመገለጫቸው አንስተዋል። በሩሲያ ላይ ህብረቱ በወሰዳቸው የማእቀብ እርምጃዎች ውጤማነት ላይ  ጥያቄ የሚያነሱ መኖራቸውን የጠቀሱት ሚስተር ቦርየል፤ በተከታታይ በተጣሉት ማ ዕቀቦችና በሩስያ ነዳጅና ጋዝ ዋጋ ላይ በተጣለው ማቀብ ምክኒያት ሩሲያ ዛሬ በበርሚል 80 ዶላር የሚሸጠውን ነዳጇን በ40 ዶላር እንድትሸጥ ተገዳለች  በማለት በሩሲያ አንጻር እየተውሰዱ ያሉትን የማቀብ እርምጅዎች ውጤታማነት አብራርተዋል። 
 ይሁን እንጂ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እያደረሰ ያለው ጉዳትና ጫና ክዩክሬንና ሩሲያ አልፎ በመላው አውሮፓ በግልጽ እየታየ ነው። ጦርነቱ እያደረሰ ካለው ኢኮኖሚያዊ ችግርና ሰባዊ ቀውስ በተጨማሪ የጦርነቱ መቆሚያ መቼ እንድሚሆን አለመታወቁ ዛሬ የአውሮፓ ዋናው አሳስቢ ጉዳይ ሁኗል። ዩክሬን ጦርነቱን በሸናፊነት ለመወጣት ያስችሉኛል የለቻቸው የውጊያ ታንኮች ባስቸኳይ እንዲያቀርቡላት የጠየቀች ቢሆንም፤ በዚህ በኩል ሁሉም የህብረቱ አገሮች ይሁንታቸውን እንዳልሰጡ ነው የሚታወቀው። አንዳንዶች በተለይ ጀርመን፤ የታንኩ እርዳታ ጦርነቱን የበለጠ እይንዳያባብሰውና ከሩሲያ ጋር ሊደረግ የሚችልን የሰላም ውይይት እንዳያርቀው በመስጋት ለመክላከል ከሚያስፈልጉ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ እርዳታዎች ውጭ በተለይ የሊዮፖልድ ሁለት የሚባሉትን የውጊያ ታንኮች ከመስጠት ለግዜው መታቀቧ እየተገለጸ ነው።፡  
ሩሲያ በበኩሏ አውሮፓውያንና ሌሎች  ለዩክሬን በገፍ የሚያቀርቡት የጦር መስሪያ ጦርነቱን የበለጠ አስከፊና አውዳሚ ከሚያደርገው ውጭ ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችልና ይልቁንም ሊያሰፋው እንደሚችል  እያስጠነቀቀች ነው።  
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰፊውን ግዜ ከወስደው የዩክሬን አጀንዳ ውጭ በፍልስጤም፣ አፍጋኒስታን፤ አርሜኒያ’ የሳህል አገሮች፣ ኢራንና ኢትዮጵያም ጭምር መወያየታቸው ታውቋል። በኢራን በተቃዋማዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ  የሚወሰደውን  የሀይል እርምጃና ግድያ ሚኒስትሮች አጥብቀው ያወገዙ መሆኑን ሚስተር ቦርየል በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት አስታወዋል። በኢራን በሚፈጸሙ የሰብዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች ተጠያቂ ናቸው ባሏቸው 37 የኢራን ባለስልጣኖችና ወታደራዊ ሹሞች ላይም የማዕቀብ ውሳኔ ተላልፏል። ይሁን እንጂ ሚኒስትሮቹ የኢራንን አብዮታዊ ዘብን በአሸባሪነት ከመፈረጅ የተቆጠቡ መሆኑ ነው የተገለጸው። 
በኢትዮጳያ ላይ በስብሰባው የሀሳብ ልውውጥ እንደተደረገ ቢታወቅም፤ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ቦርሪየል ግን በጋዜጣዊ መገለጫቸው ወቅት ያነሱት ነገር አልነበረም። ዶችቬለ  በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የፈርነሳይና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሚኒስትሮቹ ያቀረቡት ዘገባ ክነበረና ጦርነቱ እንደተጀመረ የታገደው የበጀት ድጎማ መቼ እንደሚለቀቅ ሚስተር ቦርየልን ለመጠየቅ ያደረገው ጥረት ግን በግዜ እጥረት ምክኒያት ሳይሳካ ቀርቷል። 


ገበይው ንጉሴ 
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW