1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮጳ ሕብረት እና የቻይና ጉባኤ 

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2011

ከጉባኤው በፊት ዩንከር በአውሮጳ የሚሰሩ የቻይና ኩባንያዎች የተሰጣቸው መብት ቻይና ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የአውሮጳ ኩባንያዎችም ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ አሳስበው ነበር። ቻይና በበኩልዋ በሯን ይበልጥ ክፍት በማድረግ ከአውሮጳ ህብረት ጋር ያላትን የኤኮኖሚ ትስስር እንደምታጠብቅ አስታውቃለች።

Belgien EU-China Gipfel in Brüssel
ምስል picture-alliance/AP Photo/O. Hoslet

የአውሮጳ ሕብረት እና ቻይና የኢኮኖሚያዊ ግንኙነት

This browser does not support the audio element.

የአውሮጳ ሕብረት እና ቻይና በኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸው ላይ የመከሩበት የጋራ ጉባኤ ትናንት ተካሂዶ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።  የአውሮጳ ሕብረት በሕብረቱ የመሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ቱስክ እና በህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ዦን ክሎድ ዩንከር፣ቻይና ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በሊ ኬክያን በተመራ ልዑካን የተወከሉበት ድርድር አስቸጋሪ እንደነበረ ቢገልጽም ውጤቱ ግን የሰመረ እንደሆነ ተነግሯል። ከጉባኤው በፊት ዩንከር በአውሮጳ የሚሰሩ የቻይና ኩባንያዎች የተሰጣቸው መብት ቻይና ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የአውሮጳ ኩባንያዎችም ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ አሳስበው ነበር። ቻይና በበኩልዋ በሯን ይበልጥ ክፍት በማድረግ ከአውሮጳ ሕብረት ጋር ያላትን የኤኮኖሚ ትስስር እንደምታጠብቅ አስታውቃለች። ገበያው ንጉሤ ከብራሰልስ ዝርዝሩን ልኮልናል። 
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW