1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግና የአውሮጳ ሊግ ፍልሚያዎች

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2016

በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ዛሬም ማታም ሁለት ወሳኝ ግጥሚያዎች ይኖራሉ ። በምሽቱ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረጉ ግጥሚያዎች፦ የጀርመኑ ባዬርን ሙይንሽን ከእንግሊዙ አርሰናል ጋ ይፋጠጣል ። ሌላኛው የእንግሊዝ ቡድን ማንቸስተር ሲቲ ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ጋ ይፋለማል ።

ቦሩስያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ2 በደርሶ መልስ 5 ለ4 አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜው በደረሰበት ወቅት
ቦሩስያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ2 በደርሶ መልስ 5 ለ4 አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜው በደረሰበት ወቅትምስል Thilo Schmuelgen/REUTERS

በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ዛሬም ማታም ሁለት ወሳኝ ግጥሚያዎች ይኖራሉ ። በምሽቱ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረጉ ግጥሚያዎች፦ የጀርመኑ ባዬርን ሙይንሽን ከእንግሊዙ አርሰናል ጋ ይፋጠጣል ። ሌላኛው የእንግሊዝ ቡድን ማንቸስተር ሲቲ ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ጋ ይፋለማል ። ሁለቱም ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ ይጀምራሉ ።

በትናንትናው እለት በነበሩ ግጥሚያዎች፦ አንድ ለዜሮ ሲመራ የነበረው እና አንድ ተጨዋቹን ጨዋታው በተጀመረ 29ኛ ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጣው ባርሴሎና በፓሪ ሳን ጃርሞ የ4 ለ1 ብርቱ ሽንፈት አስተናግዷል ። በደርሶ መልስ የ6 ለ4 ድልም ፓሪ ሳን ጃርሞ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፏል ። በተመሳሳይ ሰአት በነበረ ሌላ ግጥሚያ፦ ቦሩስያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ2 በደርሶ መልስ 5 ለ4 አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜው ደርሷል ። የሚያዝያ 7 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በአውሮጳ ሊግ ደግሞ፦ ነገ አታላንታና ሊቨርፑል፤ ዌስትሀምና ባዬር ሌቨርኩሰን፤ ሮማ ከሚላን እንዲሁም ማርሴይ ከቤኔፊካ ጋ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ። በተለይ በመጀመሪያ ግጥሚያው በሜዳው አንፊልድ የ3 ለ0 ሽንፈት ያስተናገደው ሊቨርፑል ብርቱ ፈተና ይጠብቀዋል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW