1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት የመሪዎች ውሳኔ እና የዩናይትድስቴትስ መመለስ

ዓርብ፣ መጋቢት 17 2013

የዓውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በዋናነት ያተኮረው በኮቪድ 19 ወረርሺና የክትባት መርሀ ግብር ላይ ሆኖ ፣ የአሜሪካ አውሮፓ ግንኑነት፣ የአውሮፓ ሩስያ ግንኑነት፤ የአውሮፓ ቱርክ ግንኑነትና ሌሎችም አለማቀፍ አጀንዳዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዚህ ስብሰባ፤ የአሜርካው ሬዝዳንት ሚስተር ጆ ባይደንም በቪዲዮ ተካፍለዋል።

Weltspiegel | 26.03.2021 | EU Gipfel mit US Präsident Biden | Tableau
ምስል EU Council/Pool/AA/picture alliance

የአውሮጳ ኅብረት ጉባኤ እና ውሳኔው

This browser does not support the audio element.

የዓውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ትናንት በቪዲኦ ተካሂዷል። ስብስባው በዋናነት ያተኮረው በኮቪድ 19 ወረርሺና የክትባት መርሀ ግብር ላይ ሆኖ ፣ የአሜሪካ አውሮፓ ግንኑነት፣ የአውሮፓ ሩስያ ግንኑነት፤ የአውሮፓ ቱርክ ግንኑነትና ሌሎችም አለማቀፍ አጀንዳዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዚህ ስብሰባ፤ የአሜርካው ሬዝዳንት ሚስተር ጆ ባይደንም በቪዲዮ ተካፍለዋል። የፕሬዝዳነት ባይደን በስብሰባው መካፈል የቀድሞው ፕሬዝዳንት  ሚስተር ትራምፕ ፖሊሲ ምክኒያት  ካውሮፓ እርቃ የነበረችው አሜሪካ የተመለስች መሆኑን የሚያበስር ሆኖ ተውስዷል። የካውንስሉ ፕሬዝዳንትና የስብሰባው መሪ ሚስተር ቻርለስ ሚሼል በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የአውሮፓ ህብረት በመደበኛው ጉባኤው የሌላ አገር መሪዎችን የሚጋብዝባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት መሆናቸውን ገልጸው፤ የዛሬው ጉባኤም ልዩ መሆኑን አውስተዋል፤ `የዛሬው ጉባኤ የተለየ ነው። ምክኒያቱም  ካስራአንድ አመት በኋላ ከፕሬዝዳንት አኦባማ ቀጥሎ ማለት ነው የአሜሪክ  ፕሬዝዳንት የተገኙበት በመሆኑ ነው። ይህም የአሜርካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና የአውሮፓ ህብረት ስለወደፊቱ ግንኑንቶቻችው ያላቸውን እይታ የሚያቀርቡበት አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን በበኩላቸው፤ አሜሪካ፤ ክነባር አጋሯ የአውሮፓ ህብረት ጋር  የኮቪድ ወረርሺኝን ለመከላከልና ለማስወገድ በሚደረው ጥረት፣ ባየር ንብረት ለውጥ፣ በላማቀፍ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች በጋራ የምትሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የአውሮፓ ህብረት መንግስታትም ካሜሪካ ጋር በበርካታ ዓለማቀፍና ሁለትዮሽ ጉዳዮች በጋራ የሚሰሩ መሆኑን በመግለጽ ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል ።

የመሪዎቹ ጉባኤ  በዋና ጀንዳቸው የኮቪድ ወረርሺንና  የክትባት ምርትና ስርጭት ጉዳዮች በስፋት ተወያይቶ፣ የበሺታውን ስርጭት ለመግታትና ክትባትን በስፋት ለመስጠት በሚቻለባቸው ሁኒታዎች ላይ መመሪያዎችን አስተላልፏል።  የስካሁኑ የክትባት አፈጻጸም ችግር የነበረበት መሆኑን የገመገሙት የህብረቱ መሪዎች፤ ክትባቱ በስፋት የሚሰጥበትን አቅጣጫ አስቀምጠዋል ተብሏል።  አገሮች የተዋህሲውን ስርጭት ለመካላከል እየወስዷቸው ያሉ እርምጃዎች እናዳሉ ሆኖ፤ ክልከላዎቹና የቁጥጥር እርምጃዎቹ  ሲነሱም ቀስ በቀስና በቅንጅት እንዲሆን ማሳሰቢያ ተስቷል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴልየን  በአሁኑወቅት የክትባቱ ሂደተ እየተፋጠነና  ለውጥም እየታየበት መሆኑን ገልጸው፤ እስካሁ የነበረውን የክትባት ሂደትም አስረድተዋል ። `አሁን የክትባቱ ሂደት እየተሻሻለና ለውጥ እየታየበት ነው። እስክሁን 88 ሚሊዮን ብልቃጦች ወይም ዶሶ ታድለው 62 ሚሊዮን  የሚሆኑት ተሰተዋል ። በዚህም በአውሮፓ ህብረት ባጠቃልይ 18.2 ሚሊዮኖችን ሁለት ግዜ ክትባት እንዲያገኙ ላማደርግ  ተችሏል` ብለዋል።

የክትባቱ ሂደት በተፈለገው መጠን ሊሄድ ያልቻለው ኩባንያዎች በውለታቸው መሰረት ማቅረብ የሚገባቸውን የክትባት መጠን ባለማቅረባቸው መሆኑን የገለጹት  ወይዘሮ ቮንደር ሌየን፤አሁን ግን አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋትና ምርቶችንም በመጨመር ለውጥ የተደረገ መሆኑንና እስከ በጋው መጨርሻም 70 ከመቶ የሚሆነው የህብረቱ ህዝብ ክትባት  እንደሚያገኝ እርግጠኝ ሁነው ተናገረዋል፡፤

ኮሚሽኑ ከህብረቱ ወደሌሎች አገሮች በተለይም ወደ ብርታኒያ የሚላኩ ክትባቶችን ወደ ህብረቱ የሚመጡት እስካልደረሱት ድረስ ሊያግድ ይችላል በማለት አቅርቦት የንበረውን ሀሳብ  ጉባኤው የመከረበት ቢሆንም፤ ህብረቱ ለሌች አገሮች የሚላኩ ክትባቶችን እንደማያግድ ግን ደግሞ ኩባንያዎች ለህብረቱና አባል አገሮች  የገቡትን ውል በማክበር ምርታቸውን በወቅቱና በትክክል ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስቧል።

የክትባትሰርቲፊኬት ወይም ፓስርትን በሚመለክትም የምሪዎቹ ጉባኤ ሀሳቡ ዜጎች በነጻና ያለስጋት ሌዘዋወሩ የሚችሉበት አሰርር መሆኑን በማመን ኮሚሽኑ በቀጣትይ ዝርዝር ሁኒታዎችን አካቶና አጥንቶ እንዲይቀርብ በማሳሳሰብ ከወዲሁ ግን ዋናውና ወሳኙ ስራ ክትባቱን በማፋጠን የተዋህሲውን ስርጭት መግታትና ወረርሺኙን ማስወገድ መሆኑን እንዳሰመረበት ተገለጹል

የመሪዎቹ ጉባኤ ከቱርክ ጋር ያለው ግንኑነት ሊሻሽል የሚችልባቸው ፕሮግርሞችን ኮሚሽኑ  አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ገምግሞ እንዲያቀርብም አሳስቧል። ከሩሲያ ጋር ስለሚኖረው  ግንኑንት ግን በስኔ ወር ምናልባትም በአካል በሚደረግ የመሪዎች ጉባኤ በጥልቀት የሚመከርበት መሆኑ ተገልጿል።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW