የአውሮፓን የመክላከያ ሀይል ለመገንባት የተጠራ ጉባኤ
ዓርብ፣ የካቲት 28 2017
የአውሮፓን የመክላከያ ሀይል ለመገንባት የተጠራ ጉባኤ
ትናንት የተጠራውና እስከ እኩለ ሌሊት የዘለቀው የ 27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት መሪዎች ልዩ ጉባኤ፤ የአውሮፓን መከላከያ በአስተማማኝ ሁኒታ ለመገንባት ያስችላል የተባለውንና በአውሮፓ ኮሚሽን የቀረበውን እቅድ በሙሉ ድምጽ የተቀበለው መሆኑ ተገልጿል።
የመክላከያው ግንባታ አስፈላጊነት
አውሮፓን እንደገና ለማስታጠቅና ለማብቃት ታስቦ በአውሮፓ ኮሚሺን የቀረበው ዕቅድ፤ ከ800 ቢሊዮን ይሮ በላይ እንደሚያስወጣ የተገለጸ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ይህን ዕቅድ በአስቸኳይ ያዘጋጀውና ያቀረበው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ለህብረቱ ሰላምና ደህንነት በአሜሪካ መተማመን ባለመቻሉ ነው ተብሏል። ቀደም ሲልም አውሮፓ የራሱ የሆነ መከላከያ ሊኖረውና ከአሜርካም ሆነ ከስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ጥገኝነት ሊላቀቅ ይገባዋል በማለት የሚከራከሩ አባል አገሮች የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ግን በተለይም ፕሬዝዳንት ትራም በዩክሬን ጉዳይ ክፕሬዝድንት ፑቲን ጋር በተናጠል ንግግር መጀመርቸው፤ በሪያድም የሁለቱ አገሮች ለኡካን ውይይት መቀጠሉ፤ እንዲሁም ከአሜሪካ ለዩኪሬን የሚስጠው ወታደራዊ እርዳታ ተገቷል መባሉ፤ አውሮፓን ፈጥኖ ወደ ራሱ መከላከያ ግንባታ እንዲገባ እንዳስገደደውና ይህ እቅድም በዚህ መንፈስ በአስቸኳይ ተዘጋጅቶ የቀረበ እንደሆነ ነው በብዙዎች የሚታመነው። በአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ ተግባራዊ የሚደረገው ዘላቂ የከተማ ልማት ለተፈናቃዮች
የዕቅዱ ማስፈጸሚያ በጀት
በኮሚሽኑ ከቀረበው የ800 ቢሊዮን ኢሮ እቅድ፤ 650 ቢሊዮኑ በአባል አገሮች በጀት የሚሸፈን ሲሆን 150 ቢሊዮኑ ደግሞ በበድር የሚገኝ ነው ተብሏ። መሪዎቹም በተለይ ፕሬዳንት ትራም በአውሮፓ ላይ እየገፉት ካለው አዲስ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፖሊሲ አንጻር እቅዱን በጥድፊያና በሙሉ ድምጽ እንዳጸደቁትና ኮሚሺኑ ዝርዝር አፈጻጸሙን ከሁለት ስምንት በኋላ በሚደረገው የመሪዎች ጉባኤ እንዲያቀርብ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል። የአውሮፓና ብሪታኒያ መሪዎች ስብሰባ በፓሪስ
የጉባኤው ውሳኔዎች ምንነትና ታሪካዊነት
ከጉባኤው ፍጻሜ በኋላ እኩለ ሌሊት ላይ የካውንስሉ ፕሬዝዳንትና የስብሰባው መሪ ሚስተር አንቶኒዮ ኮስታ ከኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንደረ ሌየን ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫ ጉባኤው የተሳክና ወሳኝ ውሳኔዎችንም ያሳላለፈ መሆኑን ገልጸዋል። “ ዛሬ ለአውሮፓና ለአውሮፕውያን ደህንነት ወሳኝ ቀን ነው። ካንድ ወር በፊት የጀመርነውን ውይይት ዛሬ ለፍሬ አብቅተነዋል፤ አውሮፓ የራሱ የሆነ መከላከያ ሊኖረው የሚችልበትን ሁኔታ ፈጥረናል” በማለት ጉባኤው ላውሮፓ ህብረት ታሪክዊ ውሳኔዎችን ያስተላለፈ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሚስተር አንቶኒዮ ውሳናዎቹን በማብራርትም ፤ መጀምሪያ የአውሮፓ የመካላከያ ኢጀንሲ ቅድሚያ በሰጣቸው መስኮች ላይ ኢንቨስት እንደሚደረግና ክዩኪሬኑ ጦርነት የተገኘውን ልምድና ክኔቶ ጋርም በመቀናጀት አስፈላጊ የሆኑ ያየርና ምድር የጦር መሳሪያዎች፤ ሚሳይሎችና የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምርቶች ላይ ትኩረት እንዲሰጥ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከግሉ ዘርፍና ከህዝቡ ተጨማሪ ገንዘብ ለማሳሰብ የታቀደ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የኮሚሺኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ፎንዴርሌየንም ጉባኤው የተሳካና ታሪካዊም እንድነበር ነው የገለጹት “ ዛሬ አዲስ ታሪክ እንደገና ተጽፏል ። ወቅቱ ለሚጠይቀው የደህንነትና መከላካያ ጥያቄ በፍጥነት መልስ የሰጠ ጉባኤ ነው።; በፍጥነትና በጋራ ኢንቨስት ለማድረግ ቁርጠኝነት የታየበት ነው። ፡ ከፓሪስ እስከ ለንደንና ብራስልስ በጋራ ለመስራትም ቁርጠ|ኝነት የታየበት ነው” በማለት በጉባኤው ስኬትና የተላለፉ ውሳኔዎች የተሰማቸውን ገልጸዋል። በለንደን የዩክሬን ደጋፊ አገራት መሪዎች ጉባኤ
በጉባኤው የተሰሙ ተጨማሪ ድምጾችና ማሳሰቢያዎች
የጉባኤው ተሳታፊዎች በማንቸውም በሩሲያና ዩክሬን የሰላም ውይይት ላይ ዩክሬንና የአውሮፓ ህብረት መሳተፍ ያለባቸው መሆኑንም አሳስበዋል። ከሀንጋሪው መሪ ሚስተር ኦርባን በስተቀርም ለዩክሬን የሚስጠጡትን እርዳታ አጠናክረው ለመቀጠል የተሳማሙ መሆኑም ታውቋል። በአሜሪካ ወታደርዊና የመረጃ ግንኙነት መቋረጥ ምክኒያት ሊፈጠር የሚቺለውን ክፍትት በመድፈን ዩክሬንን ለማገዝ የቆረጡ መሆኑንም አሳውቀዋል። ሆኖም ግን የእቅዱ ተግባራዊነት ቀላል እነደንደማይሆንና ግዜም ሊወስድ እንደሚችል የሚገመት ሲሆን፤ አውሮፓ የራሱን መከላከያ ለመግንባት የሚያደረገው ጥረት ከአሜርካ ጋር ሊያቆራርጠው እንደማይገባ በማሳሰብ ግንኙነቱን ለማሻሻልና ለማስቀጠል ጥረት መደረግ እንዳለበት የሚያሳስቡ ድምጾች ከጉባኤው ውስጥ ጭምር ተሰምተዋልም ተብሏል።
ገበያው ንጉሴ / አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ