የአውሮፓው ኅብረት የሊዝበን የውል ሰነድና ጀርመን፣5 የካቲት 2001ሐሙስ፣ የካቲት 5 2001በካርልስሩኸ ከተማ የሚገኘው የጀርመን ከፍተኛ ህገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሊዝበን፣ ፖርቱጋል ፣ የተፈረመውን የአውሮፓውን ኅብረት የሚመለከተውን ውል በመቃወም ክስ ያቀረቡ ሰዎችን አቤቱታ ከሰኞ አንስቶ እስከ ትናንት ድረስ፣ ለ 3 ቀናት ማዳመጡ ተገለጠ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግየጀርመን ህገመንግሥታዊ ፍርድ ቤት በካርልስሩኸ፣ምስል APማስታወቂያክስ ያቀረቡት በጀርመን ፓርላማ የግራ ፈለግ ተከታዩ ፓርቲ፣ የህዝብ እንደራሴዎች ተጠሪዎችና ወግ አጥባቂው የህዝብ እንደራሴ Peter Gauweiler ናቸው። የተቃውሞው ዋና ነጥብ፣ ውሉ፣ የዴሞክራሲ ጉድለት የሚታይበትና የብሔራዊ ፓርላማዎችን መብት የሚገፍ ነው፣ የሚል ነው። T Y/SL ►◄