1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ቀውስና ተጽዕኖው በአፍሪቃ

ረቡዕ፣ ኅዳር 27 2004

በአውሮፓ የጋራ ምንዛሪ ክልል በኤውሮ-ዞን ውስጥ የተፈጠረው የፊናንስ ቀውስ የአፍሪቃን ሃገራት ንግድና የኤኮኖሚ ዕድገት እንዳያሰናክል ማስጋቱን ቀጥሏል።

ምስል DW

በግዙፉ የንግድ አካባቢ በአውሮፓ ሕብረት ዓባል ሃገራትና በቀድሞዎቹ ቅኝ ግዛቶች መካከል የሚደረገው ንግድ ከ 370 ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ መሆኑን ነው የሕብረቱ መረጃ የሚጠቁመው። ይህም በቀላሉ የሚገመት አይደለም። የአውሮፓ አንድ ከመቶ ዕድገት ለአፍሪቃ 0,5 ከመቶ ዕድገት ማለት ነው። የዓለም ንግድ ድርጅት ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስካል ላሚይ ባለፈው ቅዳሜ አክራ ላይ ባካሄዱት ጋዜጣዊ ጉባዔ የአፍሪቃን የንግድ ከፍተኛ ጥገኝነት በማመልከት የአውሮፓ ኤኮኖሚ ጋብታ ለክፍለ-ዓለሚቱ ችግር መሆኑን አስረድተዋል። አፍሪቃ በረጅም ጊዜ በውስጥ ገበዮቿ ላይ ይበልጥ ብታተኩር እንደሚበጃት ነው የተመከረው። ይህ ግን ቢቀር ለጊዜው ቀላል ነገር የሚሆን አይመስልም። በጉዳዩ በስኮትላንድ ዳንዲይ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ንግድ ምሁር የሆኑትን ዶር/መላኩ ደስታን አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW