የአየር ንብረት ለዉጥና አፍሪቃ
ዓርብ፣ ጥቅምት 8 2006ማስታወቂያ
የአየር ንብረት መዛባት አፍሪቃ ዉስጥ የሚያደርሰዉን ጉዳት መቀነስ ሥለሚቻልበት ሥልት የተነጋገረ ዓለም አቀፉ ጉባኤ አሩሻ-ታንዛኒያ ዉስጥ ተደርጓል።ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ለአራት ቀናት የተነጋገረዉ ጉባኤ የአየር ንብረት መዛባት አፍሪቃ ዉስጥ በጤና፥ በምግብ አቅርቦት፥ በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያደረሰና ሊያደርስ የሚችለዉ ጉዳት ተመክሮበታል።ጉባኤተኞቹ እንዳሉት ችግሮቹን ለማስወገድ ተመራማሪዎችና መንግሥታት መዉሰድ የሚገባቸዉ እርምጃዎችም ተጠቁመዋል። የአየር ንብረት ለዉጥ ሥለሚያደርሰዉ ጉዳትና መፍትሔዉ የሚመክር ዓለም አቀፉ ጉባኤ አፍሪቃ ዉስጥ ሲደረግ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ