1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአይን ሞራ ግርዶሽ ህመም የአይን ብርሀናቸዉን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 22 2017

አርሶና ጎልጉሎ ያመርት የነበረ ገበሬ ለአመታት መዳን በሚችለዉ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህመም ምክንያት እይታዉ ሲገደብ በህክምና የዕይታ ብርሀኑ ተመልሶ ይመጣል ብሎ አያስብም ነበር ። በኢትዮጱያ ከአይን ሞራ ግርዶሽ ህመም ጋሮ በተያያዘ በርካቶች በመረጃ እጦት ምክንያት በርካቶች በተራዘመ ጊዜ የአይን ብርሀናቸዉ ሳይመለስላቸዉ ቀርቷል።

አማራ ክልል የሚገኘዉ የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ከ20 ሽህ ለሚደርሱ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን ህክምና ሲሰጥ አብዘሀኛዎቹ አርሶአደሮች ናቸ
አማራ ክልል የሚገኘዉ የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ከ20 ሽህ ለሚደርሱ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን ህክምና ሲሰጥ አብዘሀኛዎቹ አርሶአደሮች ናቸዉ።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናው ደስታችንን መልሶልናል ፤ አርሶ አደር

This browser does not support the audio element.

መዳን በሚችል የአይን ሞራ ግርዶሽ ህመም የአይን ብርሀናቸዉን የሚያጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ 

በተለይም ህክምና የማግኘት ዕድል የሌላቸዉ አርሶደሮች የችግሩ ተጠቂዎች ሲሆኑ በተራዘመ ጊዜም የአይን ብርሀናቸዉን ላይመለስ ሊያጡት ይችላሉ ተብሎል 

የቦሩ ሜዳ ሆስፒታልም 20 ሽህ ለሚደርሱ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን ህክምና ሲሰጥ አብዘሀኛዎቹ አርሶአደሮች ናቸዉ።

አርሶና ጎልጉሎ ያመርት የነበረ  ገበሬ ለአመታት መዳን በሚችለዉ የአይን ሞራ ግርዶሽ  ህመም ምክንያት እይታዉ ሲገደብ በህክምና የዕይታ ብርሀኑ ተመልሶ ይመጣል ብሎ አያስብም ነበር 

በኢትዮጱያ ከአይን ሞራ ግርዶሽ ህመም ጋሮ በተያያዘ  በርካቶች በመረጃ እጦት ምክንያት በርካቶች በተራዘመ ጊዜ የአይን ብርሀናቸዉ ሳይመለስላቸዉ ይቀራል እነኝህ አርሶደሮች ግን በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል በተደረገላቸዉ ህክምና ብርሀናቸዉ ሊመለስ ችሏል

«አርሸ ስበላ ማንም ሳይቀድመኝ አይኔ ጠፋብኝ ሀያታችሁ ይቆይ ብርሃን እንዳሳያችሁኝ ነገ በአኬራ ብርሃን የሚሆንላችሁ አላህ ያድርጋችሁ< ጎተራ የምሞላ ሰዉ ከስቤ የምበላ ሰዉ ከታመምኩ ሦስት አመቴ ነዉ ዛሬ  አይኔ ተገልፆልኛል በናንተ»

በባሕር ዳር ለ1000 ሰዎች የዓይን ቀዶ ህክምና ተደረገ

በኢትዮጵያ ከአመታት በፊት የጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መረጃ የማየት ችግር ካለባቸዉ 1.5 ሚልየን ሰዎች ዉስጥ 600 ሺህ የሚደርሱት የአይን ብርሀናቸዉን ያጡት በአይን ሞራ ግርዶሽ ነዉ ወጣት ራህመት ሀሰን የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በዚሁ ህመም የአይን ብርሃን አጥታ ቆይታለች

«ሆስፒታል ዉስጥ ሳያቸዉ ከኔ ያነሱ ልጆች አሉ እነሱን ሳይ ነዉ የተረጋጋሁት እንጂ አዕምሮየ ሌላ ሊገባ ነበር እና በጣም ነዉ ደስ ያለኝ ሁለት ልጆች አሉኝ የአምስት አመትና የዘጠኝ አመት ልጆች ያሳዝናል ደግሞ ፈጣሪ ይህንን ሲያመጣዉ ደስተኛ ነኝ»

የአይን ሞራ ግርዶሽ  ህመም በገጠር 

ከስምንት አመታት በኃላ የአይናቸዉ ብርሃን ዳግም የተመለሰላቸዉ ሽህ ደረሰ ደሳለዉ ዛሬ ላይ በህክምና የአይን ብርሃናቸዉ መመለሱን ይገልፃሉ

«ግራ አይኔን ከሻርኩኝ ዘንድሮ ስምንቶ አመቴ ነዉ ዘንድሮ በዘጠነኛዉ አመት ቀኞ አይኔ ተሸፍኖ አስቀርቶኝ እምባ እየኮተረ አላሳየኝ ሲል ዛሬ የምስራች እናንተ ሀያት ይስጥልኝ አይኔ ተገለፀ»

አሁን የተደረገላቸዉ የአይን ብርሃን የመመለስ ህክምና በቀጣይ በእርሻ ስራ ላይ በሚኖራቸዉ ተግባር እንደሚያግዛቸዉ ይናገራሉ አርሶደሮቹ

«ትናንትና ታክሜ እዚህ ቅድድ ሲያደርጉት ፖሊስ መኪናዉም ሰዉም ታየኝ ይህ የጌታ ስራ ነዉ  ተመልሸ የግብር መሬቴ ላይ ስደርስ እንዴት ነዉ ጥቅሙ እንግዲህ»

 

በጀርመን ድርጅት የሚደገፈዉ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ታካሚዎች

የአይን ሞሬ ግሮዶሽ  በህፃናትና ወጣቶች ላይ

በእድሜ መግፋት በብዛት የሚከሰተዉ ህመሙ አልፎ አልፎ በወጣቶችና ህፃናት ላይ ይከሰታልባለፉት ሰባት አመታትም የቦሩ ሜዳ ሆስፒታሎ 20000  ለሚደርሱ የአይን ብርሃን እይታቸዉ ለተጋረደባቸዉ ሰዎች ህክምና መስጠቱን የሆስፒታሉ ስራአስኪያጂ አቶ ሲሳይ ተበጀ ይናገራሉ

«ከ20000 በሌይ የህብረተሰብ ክፍል ከአይነስዉርነት አድነናል በነፃ የሚመጡበት የሚሄዱበት ትራንስፖርት እዚህ ቁርስ ምሳ እራት በነፃ ነዉ ድርጂቱ ነዉ የሚችለዉ ኪዮር ብላይንድነስ ፕሮጀክት በመተባበር»

በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል የሚካሄደዉ ግጭት በሆስፒታሉ ስራ ላይ ተፅኖ ባያሳድርም ህሙማኑ ግን መንገድ ይዘጋባቸዋል

«እኛ ጋር ተፅኖ አልፈጠረም ሲመጡ ግን የመንገድ መዘጋጋት አለ ያዉ ህብረተሰቡ ደግሞ ህመም ስለሆነወደ ሆስፒታል ሄዶ ይታከማል

 

የአይን ብርሃን ለሌላቸዉ ህጻናት ብቸኛዉ ህጻናት መዋያ በአዲስ አበባ

የአይን ህክምና ተቋማት በበቂ አለመኖር 

እየተባባሰ የመጣዉ የአይን ሞራ ግርዶሽን ለመከላከል በቂ የህክምና ተቋማት አለመኖር ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሰዉ የችግሩ ተጠቂ መሆን የዘርፉ ተግዳሮት መሆኑ ተገልፆል

«የአይንህክምና በመሰረቱ የተስፋፋ አይደለም በየወረዳዉ በየሆስፒታሉ አይደለም አገልግሎቱ የሚሰጠዉና በአብዘሀኛዉ ከምስራቅ አማራ ዉጭ ይመጣል ሰዉ ህመሙ እየጨመረ የሄደዉም በዚህ ምክንያት ነዉ»

ኢሳያስ ገላው 

ታምራት ዲንሳ 

ጸሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW