1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚኢትዮጵያ

የአደባባይ ኢፍጣርና ርዳታ በድሬዳዋ

ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2016

በከተማዋ በተለምዶ ለገሀር አደባባይ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ትናንት በተዘጋጀው የአፍጥር ዝግጅት ላይ ለዶይቼ ቬለ በሰጠው አስተያየት ከአደባባይ አፍጥሩ በተጨማሪ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መስራታቸውን ገልጿል

በኢፍጣሩ ሥነሥርዓት ላይ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል
 የድሬደዋ ከተማ ሙስሊሞች የረመዳንን ፆም  አጋማሽ  ምክንያት በማድረግ በአደባባይ ሲያፈጥሩምስል Mesay Tekilu/DW

የአደባባይ ኢፍጣርና ርዳታ በድሬዳዋ

This browser does not support the audio element.

 የድሬደዋ ከተማ ሙስሊሞች የረመዳንን ፆም  አጋማሽ  ምክንያት በማድረግ የአደባባይ ላይ አፍጥር አደረጉ።በከተማዋ ሙስሊም ወጣቶችና በተለያየ አካላት ትብብር ከተዘጋጀው የአደባባይ (የጎዳና) አፍጥር ጎን ለጎን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች  የምግብ እና ሌሎች ድጋፎች መሰብሰቡን የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።1445ኛዉ የረመዳን ወር ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በወጣቶች እና ሌሎች አካላት ትብብር ድጋፍ ያገኙ ወገኖች በችግራችን ወቅት ደርሰውልናል ላሏቸው ምስጋና አቅርበዋል።የዒድ ጥሪ ለዲያስፖራ ማህበረሰብ

                                         የተረጂዎች ምስጋና 

በከተማዋ መስተዳድር ፣ በወጣቶች እና ሌሎች አካላት ትብብር ድጋፍ ከተደረገላቸው ነዋሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ኤልያስ ሙሜ በችግር ጊዜ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወ/ሮ ዘምዘምም በተመሳሳይ የተለያየ የምግብ ድጋፍ በመስጠት ለችግራችን ደርሰውልናል ያሏቸውን አመስግነዋል።

በኢፍጣሩና በእርዳታ ማሰባሰቡ የአደባባይ ዝግጅት በርካታ የድሬዳዋ ከተማ ሴቶችም ተካፋዮች ነበሩምስል Mesay Tekilu/DW

 

                  የድግሱና የርዳዉ አሰባሳቢ ወጣቶች

ወጣት ፊላ አህመድ በከተማዋ በተለምዶ ለገሀር አደባባይ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ትናንት  በተዘጋጀው የአፍጥር ዝግጅት ላይ ለዶይቼ ቬለ በሰጠው አስተያየት ከአደባባይ አፍጥሩ በተጨማሪ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መስራታቸውን ገልጿል ።ሌላኛዋ ወጣት ቢፍቱ አህመድም ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ተግባር ማከናወናቸውን ገልፃለች።የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ትናንት በድሬደዋ የተከናወነውን የአደባባይ አፍጥር እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የሚያስፈልገውን ድጋፍ በማሰባሰብ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ።መስቀል አደባባይና የጎዳና ኢፍጣር ዝግጅት ውዝግብ

 

በኢፍጣሩ ሥነሥርዓት ላይ የመግሪብ ሶላት በጋራ ሲሰገድምስል Mesay Tekilu/DW

በድሬደዋ የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የፋሲካ እና የረመዳን የፆም ወቅት መጀመሩን ተከትሎ በከተማዋ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ የህብረተሰቡን የእርስ በእርስ መደጋገፍ እና  አንድነትን ለማጠናከር የሚረዱ ተግባራት በሁለቱም እምነት ተከታዮች በመካሄድ ላይ ናቸው።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW