የአዲስ አበባዉ የጀርመን ት/ቤት የመጀመርያ ተመራቂ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 15 2007ማስታወቂያ
የዛሬ 60 ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ላይ የጀርመን ትምህርት ቤት በተቋቋመ በሁለተኛ ዓመቱ ከአራተኛ ክፍል ትምህርታቸዉን ጀምረዉ እዝያዉ የሁለተኛ ደረጃ ትምርታቸዉን ካጠናቀቁት የመጀመርያዎቹ ብቸኛ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች መካከል ዶክተር ካሳይ ወልደ ጊዮርጊስ የሰጡን አስተያየት ነበር። በኬሚስትሪ ትምህርት በጀርመን ሃገር የዶክትሪት ማዕረግን ያገኙት አቶ ካሳይ ወልደጊዮርጊስ ዛሬ በኢትዮጵያና በጀርመን ሃገር መካከል ድልድይን ዘርግተዉ የቀድሞዎቹን ተማሪዎች በማገናኘት በሃገራቱ መካከል ያለዉን የቆየ የባህል፣ የእዉቀት ብሎም የኤኮኖሚ ትስስር ይበልጥ እንዲጠነክር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የአዲስ አበባዉ የጀርመን ትምህርት ቤት ከዛሬ ከስድሳ ዓመት በኋላ በምን ደረጃ ላይ ይገኝ ይሆን? በርግጥ በኢትዮጵያ ዉስጥ የጀርመንኛ ቋንቋን የሚናገር ማኅበረሰብ በርከት ብሎስ ይሆን?! የጀርመንን እዉቀት ቀስመዉ ኢትዮጵያዉያ ዉስጥ በማገልገል ላይ ያሉ ዜጎችስ ቁጥር ምን ያህል ይሆን። በለቱ ዝግጅታችን ስድሳ ዓመት የሆነዉን የጀርመን ትምህርት ቤት ይዘን የመጀመርያዉን የትምህርት ቤቱን ተመራቂ በእንግድነት ጋብዘናል።