1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ስታዲየም ማሻሻያ ከ3 ወራት ባልበለጠ ጊዜ ይጠናቀቃል ተባለ

ረቡዕ፣ ኅዳር 19 2016

የአዲስ አበባ ስታዲየምን ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አሟልቶ ለማጠናቀቅ ቀሪ ሥራዎች ከሦስት ወራት በላይ እንደማይፈጅ በባሕል እና ስፖርት ሚንስትር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ዐስታወቁ ። ሚኒስቴር ዴኤታው በተለይ ከዶይቸ ቬለ (DW) ጋ ዛሬ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፦ ይህ ግምታዊ ሐሳባቸው መሆኑንም አክለዋል ።

የአዲስ አበባ ስታዲየም ። ፎቶ፦ ከማኅደር
የአዲስ አበባ ስታዲየም መስፈርቶችን አላሟላም በሚል ጨዋታ እንዳይካሄድበት በካፍ ከመታገዱ በፊት የዛሬ 3 ዓመት የኢትዮጵያ እና የዛምቢያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ሜዳ ላይ ተሰልፈው ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Omna Tadele/ DW

የአዲስ አበባ ስታዲየምን ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አሟልቶ ለማጠናቀቅ ቀሪ ሥራዎች ከሦስት ወራት በላይ እንደማይፈጅ በባሕል እና ስፖርት ሚንስትር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ዐስታወቁ ። ሚኒስቴር ዴኤታው በተለይ ከዶይቸ ቬለ (DW) ጋ ዛሬ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፦ ይህ ግምታዊ ሐሳባቸው መሆኑንም አክለዋል ። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም አስፈላጊ የሚባሉ የማሻሻያ ሥራዎች ተጠናቀው የሜዳ ሣርን የማሻሻልን የመሳሰሉ የማሟያዎች፤ ባለሥልጣኑ እንዳሉት «ጥቃቅን» ሥራዎችን ለመፈጸም ርብርብ እየተካሄዱ መሆኑን ገልጸዋል ። በኢትዮጵያበሌሎች ከተሞችም ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገም ነው ብለዋል።  አዲስ አበባ ስታዲየምን በጀት መድቦ እየሠራ የሚገኘው ፌዴራል መንግሥት መሆኑን ጠቅሰዋል ።  የድሬዳዋ ስታዲየም በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ወጪ እየተሠራ በጥሩ ሁኔታ ላይ ከሚገኙት መካከል አንዱ ነው ብለዋል ። በሐዋሳ እና አሦሳ «አንዳንድ እንቅስቃሴዎች አሉ» ያሉት ባለሥልጣኑ፦ ቃሊቲ አካባቢ ያለው የቃሊቲ ስታዲየም በአዲስ አበባ መስተዳደር «ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት» እየተሠራ፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል ። የባሕርዳር ስታዲየምን የሚሠራው የአማራ ክልል «ራሱ በጀት መድቦና አጋር አስተባብሮ» መሆኑን ገልጸዋል ።  

የአዲስ አበባ ስታዲየም መስፈርቶችን አላሟላም በሚል ጨዋታ እንዳይካሄድበት በካፍ ከታገደ ዓመታት ተቆጥረዋል ። እገዳው ከተላለፈ ከሁለት ዓመታት በላይ ማለፉ ይታወቃል ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Omna Tadele/ DW

አደይ አበባ ስታዲየምን በተመለከተ፦ «መንግሥት ተጨማሪ ድጋፍ በማፈላለግ ላይ» እንደሚገኝ ይፋ አድርገዋል። «ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ በጣም ተወዳዳሪ እና  በቁጥር ከሦስት እስከ አራት የተጠናቀቁ ጥሩ ስታዲየሞች ባለቤት» መሆን እንደሚቻልም አክለዋል ። «በምንም አይነት ችግር ውስጥ ብንሆንም መንግሥት ለዘርፉ በጀት መድቦ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን «ላረጋግጥልህ እወዳለሁ» ብለዋል ። 

ባለፉት ጊዜያት እግር ኳስን ጨምሮ ለስፖርት መሠረተ ልማት ማዘውተሪያዎች የተሠሩ ሥራዎች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አለማሟላታቸው ችግር ፈጥሮ መቆየቱን ሚንስትር ዴኤታው ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ስታዲየሞች በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አያሟሉም በሚል ካፍ ጨዋታ እንዳይካሄድባቸው እገዳ ካስተላለፈ  ከሁለት ዓመታት በላይ ማለፉ ይታወቃል ። በእነዚህ ጊዜያት ብሔራዊ ቡድኑ በሀገር ውስጥ በሜዳው ሊያደርጋቸው የሚገቡ ጨዋታዎችንወደ ሌሎች ሃገራት እየተጓዘ ለማካሄድ ተገድዷል ። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መጐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW