1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ ኢሬቻ በዓል ዝግጅት ምን ይላሉ?

ዓርብ፣ መስከረም 25 2016

አዲስ አበባ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ሽር ጉድ እያለች ነው። የዋና ከተማዋ ፖሊስ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደውን ጨምሮ “በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት” አስራ አራት መንገዶች መዘጋታቸውን አስታውቋል። የዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ስለ በዓሉ ዝግጅት ምን ይላሉ?

የኢሬቻ በዓልን ለመሳተፍ አዲስ አበባ የደረሱ እንግዶች
አዲስ አበባ የኢሬቻ በዓል ተሳታፊ እንግዶቿን በዕለተ አርብ እየተቀበለች ትገኛለች። ምስል Seyoum Getu/DW

የሕዝብ አስተያየት፦ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ ኢሬቻ በዓል ዝግጅት ምን ይላሉ?

This browser does not support the audio element.

በነገው እለት በአዲስ አበባ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ-ፊንፊኔ ክብረ በዓል ለማክበር እንግዶች በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መዲናዋ እየተመሙ ነው።  
አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለጸጥታ ጥበቃው ሲባል በተለይም በዓሉ ወደ ሚከበርበት መስቀል አደባባይ እና ስታዲየም የሚወስዱ በርካታ መንገዶች ተዘግተዋል።

የ2015 ዓ.ም. የኢሬቻ ሆራ ሀርሰዲ በቢሾፍቱ ዛሬ ተከበረ

በዚህ በዓል መዳረሻ ከመንገዶች መዘጋጋት ጋር ተያይዞ የእለት ህይወቱ በእግር ረዘም ያሉ መንገዶችን ከመጓዝ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች የሚፈተኑ እንዳሉ ተጠባቂ ነው፡፡ በዓሉ በሰላም ተከብሮ ይጠናቀቅ ሆን በሚል ስጋት ውስጥ የሚገቡ የማህበረሰብ አካላትም አይታጡም።

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ አከባበር

የበዓሉ ታዳሚዎች በስፋት ወደ ከተማዋ ከመግባታቸው አንጻር እድሉን ወደ ንግድ ቀይረው ለመጠቀም በዓሉን በጉጉት የሚጠብቁም በርካቶች ናቸው። ሥዩም ጌቱ በመዲናዋ ጎዳና ላይ ዞር ዞር ብሎ ከነዋሪዎች አስተያየት አሰባስቧል፡፡ ከሕዝብ የተሰበሰቡትን አስተያየቶች ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

ሥዩም ጌቱ 
እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW