1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ነዋሪ ተቃዉሞና ጥያቄ 

ሰኞ፣ መስከረም 7 2011

በአዲስ አበባና  አካባቢዋ ላይ በተከሰተው ሁከት በመቃወም በሽዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመዲናዋ የተለያዩ ቦታዎች ዛሬ ቁጣቸዉን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል። ሰልፈኞቹ በአብዛኛዉ « አንድ ሕዝብ አንድ ኢትዮጵያም» ሲሉ ነዉ የተደመጡት።

Äthiopien Addis Abeba, Unruhen
ምስል DW/B. ze Hailu

ተቃውሞ በአዲስ አበባ

This browser does not support the audio element.

ለጥቃቱ እጃቸው አለበት የተባሉ ከ600 መቶ የሚበልጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ከጥቂት ሰዓታት በፊት በሰጡት መግለጫ አሳዉቀዋል። ግጭትና ግድያዉ አገሪትዋ የጀመረችዉ ለውጥ እንዳይሳካ ለማድረግ ሰፊ በሆነ እቅድ ተዘጋጅቶ ታስቦበት የተከናወነ እንደሆነና ግን የጸጥታ ኃይሎች ባደረጉት ርብርብ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ተናግረዋል። ከአለም ዜና እንደተከታተላችሁት  በሳምንቱ መጨረሻ በቡራዩ አካባቢና በአንድ አንድ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች በተከሰተ ብሔር  ተኮር ግጭት ከሀያ የሚበልጥ ሰው መሞቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታዉቆአል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ  በግጭቱ 23 ሰው መሞቱን ቢያረጋግጡም፣ የሟች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ነዉ የተገለፀዉ።

ጌታቸዉ ተድላ 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW