1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ጸጥታና የሚታሰሩ ወጣቶች ጉዳይ

ዓርብ፣ መጋቢት 9 2014

ከአድዋ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ውስጥ ብዙ ወጣቶች በጅምላ እየተያዙ እየታሰሩ መሆኑ ተነገረ። ኢዜማ ድርጊቱ የከተማው ወጣት ሀሳብ እንዳይሰጥ፣ እንዳይቃወም ለማሸማቀቅ ነው ብሏል። ባልደራስ በበኩሉ ታሳሪዎቹ በምግብ ፣ በመድኃኒት እና በውኃ እጦት እንዲማረሩ እየተደረገ ነው፤ በዚህም ከፖለቲካ ተሳትፎ እንዲርቁ እየተሠራ ነው ብሏል።

Äthiopien Stadtbild Adis Abeba mit Schriftzug
ምስል Seyoum Getu/DW

ኢዜማ እና ባልደራስ የወጣቶቹን እስር ተችተዋል

This browser does not support the audio element.

 

ከአድዋ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ውስጥ ብዙ ወጣቶች ምስላቸው ከማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች እየተፈለገ እና በዕለቱ በተለያዩ ቦታዎች የመንግሥት ሰዎች ባስቀመጥዋቸው ካሜራዎች በተቀጹ ምስሎች ደጋፊነት በጅምላ እየተያዙ እየታሰሩ ነው ተባለ። ይህንን ያለው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ( ኢዜማ )ድርጊቱ የከተማው ወጣት ሀሳብ እንዳይሰጥ፣ እንዳይቃወም ለማሸማቀቅ ነው ብሏል። የከተማዋ ወጣት አንገቱን እንዲደፋ እየተደረገ ነው ያለው ኢዜማ ታሳሪዎቹ እንዲፈቱ ፣ ወንጀል ሰርተዋል ከተባለም በግልጽ ለፍትሕ እንዲቀርቡ ጠይቋል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በበኩሉ ከሰሞኑ ታስረው አባ ሳሙኤል የተባለው እሥር ቤት የተወሰዱ ወጣቶች በምግብ ፣ በመድኃኒት እና በውኃ እጦት እንዲማረሩ እየተደረገ ነው በዚህም ከፖለቲካ ተሳትፎ እንዲርቁ እየተሠራ ነው ብሏል። ከታሰሩት ወጣቶች መካከል 20 ዎቹ ትናንት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲመጡ ከተደረገ በኋላ ዛሬ ጥዋት ቤታቸው እንዲበረበር ተደርጓልም ብሏል። የደንብ ጥሰት ፈጽመዋል ያላቸውን 146 አባላቱን እንዳሰናበተ የተናገረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚታፈስ ወጣት የለም በማለት እሥሩን በተመለከተ ለሚቀርበው ቅሬታ ትናንት ምላሽ ሰጥቷል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW