1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስታወቀ

እሑድ፣ ሰኔ 13 2013

ዓለምም የኢትዮጵያ ህዝብም ያተኮረበት ከሁለት ቀናት በኋላ የሚካሂደው ስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

Äthiopien Wahlkampf in Addis Abeba
ምስል Negash Mohammed/DW

ዓለምም የኢትዮጵያ ህዝብም ያተኮረበት ከሁለት ቀናት በኋላ የሚካሂደው ስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስታወቀ።የኢዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ  ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር የከተማይቱን ጸጥታ ለማስጠበቅ በደንብ ተዘጋጅቷል።
ኮማንደር ፋሲካ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣የወቅቱን የፀጥታ ሁኔታና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ ያስገባ ያሉትን እቅድ ማውጣቱን ፣ እያንዳንዱ የፖሊስ አባልም ስለ እቅዱ ግንዛቤ እንዲጨብጥ መደረጉን ተናግረዋል።ፀጥታ አስከባሪዎች መከተል ያለባቸው፣ የአሰራር ስርዓትና የስነ ምግባር መመሪያም ተዘጋጅቷል ብለዋል  ኮማንደር ፋሲካ ፣ፖሊስ «ድምጽ ለመስጠት የሚመጣውን ህዝብ ትኩረት የሚስብና የስነ ልቡና ጫና ሊፈጥር የሚችል ካሉት የተለየ እንቅስቃሴ መቆጠብ እንዳለበት ፣ለምርጫ አስፈጻሚዎችም መመሪያ ወይም ምክር መስጠት እንደማይችልም ገልጸዋል።

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW