የአዲስ ዓመት ተስፋ በትግራይ
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2018
ማስታወቂያ
የአዲስ ዓመት ተስፋ በትግራይ
የተገባደደው 2017 ዓመተ ምህረት በትግራይ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውሶች፣ የፀጥታ ስጋቶች፣ ክፍፍል (የህወሓት እና የታጣቂዎች) የታየበት ዓመት ሆኖ አልፏል። ለዓመታት ክልሉን የመራው ህወሓት ለሁለት መከፈሉ ተከትሎ ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና የድህንነት ስጋት ተፈጥሮ ቆይቷል። በእነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች ዜጎች ዓመቱን በጦርነት ስጋት ውስጥ አሳልፈውታል። ከትግራይ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በአዲሱ ዓመት ሰላም፣ የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ይመኛሉ። በትግራይ ደቡባዊ ዞን እየበረታ የመጣዉ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት
የተጠናቀቀ 2017 ዓመተምህረት በትግራይ በርካታ የሚባሉ ታሪካዊ ሁነቶች የታዩበት፣ ከምንም በላይ ደግሞ በፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ተሁኖ ያለፈ ዓመት ተደርጎ በበርካቶች ይታወሳል። የሃምሳ ዓመት ዕድሜ ያለው ህወሓት በውስጡ የተፈጠረው ክፍፍል ተከትሎ፥ የዚሁ ክፍፍል ተቀጥያ የሆኑ ልዩነቶች በሲቪል እና ወታደራዊ ተቋማት የተከሰተበት ዓመት ነበር፥ የተገባደደው 2017 ዓመተምህረት። ህወሓት እና የፌደራል መንግስት ወደ ሌላ ዙር ፍጥጫ እንዳይገቡም ከፍተኛ ስጋት በበርካቶች ተፈጥሮ ዓመቱ አልፏል። ከመቐለ እና ሌላ የትግራይ አካባቢዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የሚናገሩትም ይህንኑ ነው።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ