1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአድዋ ድልን አከባበር አድማስ ለማስፋት ያቀደው መድረክ

ሐሙስ፣ የካቲት 23 2015

127 ኛውን የአድዋ ድል በአል አስመልክቶ «አድዋ ፓን አፍሪቃ ፎረ» ም በሚል ወጣቶች እና ቢዝነስን ማዕከል ያደረገ የፓናል ውይይት በ አዲስ አበባ እና በደቡብ አፍሪቃ ኬፕታውን ከተማ ትናንት ተካሄድዋል።

Äthiopien Addis Abeba Adwa Sieg
ምስል Solomon Muche/DW

የአድዋ ድልን አከባበር አድማስ ለማስፋት ያቀደው መድረክ

This browser does not support the audio element.

127 ኛውን የአድዋ ድል በአል አስመልክቶ «አድዋ ፓን አፍሪቃ ፎረ» ም በሚል ወጣቶች እና ቢዝነስን ማዕከል ያደረገ የፓናል ውይይት በ አዲስ አበባ እና በደቡብ አፍሪቃ ኬፕታውን ከተማ  ትናንት ተካሄድዋል። የመድረኩ አላማ የአድዋ ድል መታሰቢያን በተለመደው ውስን መንገድ ከማክበር ይልቅ አህጉር አቀፍ ድል እንደመሆኑ አድማሱን ማስፋት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ለዚህም አድዋ ለአፍሪቃ ድል መሠረት ሆኖ ከሀገር አልፎ በአህጉር ደረጃ እንዲከበር በአርቲስት ቻቺ ታደሰ እና በ ፍቅር ይሁን አዘጋጅነት የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ እና በኬፕታውን በተመሳሳይ መልኩ ቀርቧል።  

በዚህ  የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ዲፕሎማቶች የአፍሪካ ማኅበረሰብ እና በውጪ ሃገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገኝተውበታል። አዘጋጁ አቶ ፍቅር ይሁን በላይ ለ ዶቼ ቬለ/ DW/፤ «ዳግማዊ አፂ ምኒሊክ  ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ነፃ ያወጡት ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሀዝቦችን ሁሉ ነው። ያን ጊዜ በተደረገ ተጋድሎ ከነጭ የበላይነት እና ከቅኝ ግዛት ነፃ እንድንሆን አድርገውናል። አሁን ደሞ እኛ መላው አፍሪቃውያን ይህንን የተሰጠንን የማንነት ድል መሠረት በማድረግ አፍሪቃን ከድህነት እና ከችግር ነፃ ልናወጣ ይገባናል» በሚል መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ይህ «አድዋ ፓን አፍሪቃን ፎረም» ዘንድሮ ለሁለተኛ ግዜ የተዘጋጀ ሲሆን ባለፈው ዓመት ለአፍሪቃ የሠሩ ብርቱ ሰዎች በሚል የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሣህለወቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለየያዩ አፍሪቃውያን ባለሙያዎችን ሸልሟል።

ዘንደሮ በተመሳሳይ ሰአት በተመሳሳይ መልኩ ደቡብ አፍሪቃ ኬፕታውን እና አዲስ አበባ የሚከበረው ይህ አድዋ ፓን አፍሪቃ ፎረም ወደፊት በመላው አፍሪቃ ከተሞች በመዘዋወር የሚከበር እንደሚሆን አዘጋጆቹ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በየዓመቱ የምታከብረው የአድዋ በአል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሀዝቦች ድል እንደመሆኑ መጠን በአሉም ይህንን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እየሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW