የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በማንቸስተር
ማክሰኞ፣ ግንቦት 15 2009ማስታወቂያ
የማንቸስተር ፖሊስ እንዳስታወቀው፣ አጥፍቶ ጠፊው ራሱ የሰራውን ቦምብ ብዙዎች የሙዚቃ ትርዒት ለማየት በተሰበሰቡበት 21,000 ሰው በሚያስተናግደው የ«ማንቸስተር አሬና» አፈንድቷል። የታዋቂዋ ወጣት ድምፃዊት አርያነ ግራንዴ የሙዚቃ ትርዒት ካበቃ በኋላ ትናንት ሌሊት ከባድ ፍንዳታ መሰማቱን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመልክተዋል። የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ ፍንዳታውን « የአሸባሪዎች ጥቃት» ማለታቸው እና የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ መጥራታቸው ተሰምቷል። በርካታ ፓርቲዎች እጎአ የፊታችን ሰኔ ስምንት ፣ 2017 ለሚካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የሚያደርጉትን የምርጫ ዘመቻ አቋርጠዋል። ፍንዳታውን ተከትሎ የፀጥታ ጥበቃው የተጠናከረ ሲሆን፣ ከመላ ዓለም የሀዘን መግለጫ በመላክም ላይ ነው።
አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ