1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ

«የአጭበርባሪው በቀል»ድራማ

ቅዳሜ፣ ጥር 4 2016

ይህ በዲጂታል ግንዛቤ ላይ የሚያተኩር እና እያዝናና የሚያስተምር አዲስ የዶቸ ቬለ በማድመጥ መማር ተከታታይ የራዲዮ ድራማ ነው። ታሪኩ ኢንዙና በተባለች ታላቅ አፍሪካዊት ምናባዊ ከተማ ይከናወናል።

የአጭበርባሪው በቀል

ክፍል 1«የመጨረሻው መጀመሪያ»

This browser does not support the audio element.

በኢንዙና ምናባዊ ከተማ በየግላቸው ኑሮን መቋቋም እንደማይችሉ ተረድተው ወጪያቸውን የሚጋሩና አብረው የሚኖሩ ሦስት የወንድማማቾች ልጆችን እንተዋወቅ። ጀምበሬ፣ እምነት እና ራሒም የወንድማማች ልጆች ቢሆኑም በባህሪያቸው እንደ ቀን እና ጭለማ የተለያዩ ናቸው። ጀምበሬ ወጣ ወጣ ማለት የምትወድ ነጻ መንፈስ ያላት ነች። ራሒም በአንጻሩ በራሱ ሐሳብ የሚመሰጥ እና ማኅበራዊ ግንኙነት ግራ የሚያጋባው ነው። እምነት ኢንተርኔት በጣም ትወዳለች። ይህ መውደዷ ሱስ ሳይሆንባት ሁሉ አልቀረም። በዚህ የአጭበርባሪው በቀል የተሰኘው ተከታታይ የራዲዮ ድራማ አንድ ፍቅር የደቆሰው ወጣት እንዴት ኮምፒውተሮች በመሰርሰር፣ በማጭበርበር እና ስም በማጥፋት እነዚህን የወንድማማቾች ልጆች እንደሚበቀል  እንሰማለን።  እነሱም ራሳቸውን ለማስከበር  ግብግብ ይገጥማሉ። ትግሉ የት ያደርሳቸው ይሆን?

 

ደራሲ: ጀምስ ሙሀንዶ (ኬንያ)

ትርጉም : እሸቴ በቀለ

ፕሮዲውሰር : ልደት አበበ / ሃና ደምሴ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW