የአፋር ዲያስፖራ ማኅበረሰብ የተቃውሞ ሰልፍ በብራስልስ
ረቡዕ፣ ጥር 25 2014
ማስታወቂያ
መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)እና የትግራይ ኃይሎች በአፋር ክልል ውስጥ የሚያደርሱትን ጥቃት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ችላ ብሏል ሲሉ የአፋር ዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ብራስልስ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አካኼዱ። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ተወካይ አቶ ሀጋር ሐማድ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትም በአፋር ክልል ጉዳይ ቸልተኝነት ታይቶበታል ሲሉ ቅሬታ እንደተሰማቸው ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ምዕራቡ ዓለም ወደ ትግራይ ክልል መንገዶች ተዘጉ ሲል አፋር ውስጥ በሕወሓት የሚፈጸመውን ጥቃት ግን ችላ ብሏል ሲሉም ተቃውሞዋቸውን ገልጠዋል። ከሰልፉ በኋላ ብራስልስ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች እና በአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ከሚለከታቸውም ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውንም አቶ ሀጋር ሐማድ ተናግረዋል።
ማንጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ