የአፍሪቃውያን ስደተኞችመከራ በሊቢያ
ረቡዕ፣ የካቲት 23 2003ማስታወቂያ
ማንተጋፍቶት ስለሺ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ Jemini Panday ን አነጋግሮ የሚከተለውን አጠናቅሯል። ሊቢያ ውስጥ ቢያንስ 1,5 ሚሊዮን ስደተኞች እንደሚጊኙ በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባዩዋ ጄሚኒ ፓንዳይ በተለይ ለዶቼ ቬሌ የአማርኛው ክፍል ገለፁ። ከነዚህ ስደተኞች መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በታች ካሉ ህገራት የፈለሱ ስደተኞች በሊቢያ ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ይታወቃል። በተለይ ይላሉ ቃል አቀባዩዋ፤ በተለይ ጥቁር አፍሪቃውያኑ በቅጥረኝነት አገልግለዋል በሚል ነው ጥቃት እየተፈፀመባቸው ያለው።