የአፍሪቃውያን ወጣቶች ሕይወት በጀርመን
ዓርብ፣ ሐምሌ 23 2013ማስታወቂያ
ዴሞክራሲያዊ መብቶችና የሕይወት ስኬት አማራጮች ሰፍነውባቸዋል ወደሚሏቸው አሜሪካና ምዕራባውያን ሃገራት እንዲህም ወደ መካከለኛው ምሥራቅም ይጓዛሉ። ይህ የስደት ማዕበል ምንም እንኳ አያሌ ወገኖችን ካለሙትና ካሰቡት ሳያደርስ ሕይወታቸውን ለባሕር ሻርክ፣ ለበረሃ የአውሬ ቀለብና ሰብአዊነት ለጎደታቸው ሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ጭምር የሰውነት አካላቸውን መገበራቸው በአሳዛኝነቱ ቢወሳም ዛሬም እንደ አፍሪቃ ካሉ ደሃ ሃገራት የኑሮ ችግርንና የአምባገነን መንግሥታትን ጭቆና ሽሽት ዕድል ዕጣ ፈንታችንን እንሞክር በሚል ዜጎች የትውልድ ቀያቸውን ለቀው፣ ያላቸውን ሃብትና ንብረት ሸጠው ካልሆነም ተበድረው ከመሰደድ ዛሬም አልተቆጠቡም። በርካታ ውጣ ውረድና ፈተናን ተቋቁሞ ካሰበው ሃገር የደረሰም አንዳንዱ የተሰደደበትን ዓላማ ሳይዘነጋ የራሱንም የቤተሰቡንም ሕይወት ሲለውጥ ገሚሱም የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ማግኘቱ አልሳካ ብሎት አልያም በብርቅርቁ ዓለም ተማርኮና ተሸንፎ በጎዳናዎችና በየማረሚያ ቤቱ ወድቆ ሀገሩን የለቀቀበትን ቀን እያማረረ ሲማቅቅ ማየት ሌላው የስደት ሕይወት አስከፊ ገጽታ ነው። እንዳልካቸው ፈቃደ በከወጣቶች ዓለም በጀርመን የአፍሪቃውያንን ተሞክሮ ያስቃኛል። ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፤
እንዳልካቸው ፈቃደ
ሸዋዬ ለገሠ