የአፍሪቃ ህብረት ወደ ቡሩንዲ ጦር እንዲላክ ጠየቀ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 6 2008ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ህብረት የሰላም እና ፀጥታው ምክር ቤት ወደ ቡሩንዲ በአፋጣኝ ወታደሮች እንዲላኩ ዛሬ ሀሳብ አቀረበ። ህብረቱ በሃገሪቱ አመፅ በሚፈፅሙ ላይም ማዕቀብ እንደሚጥል ምክር ቤቱ ገልጿል። ህብረቱ አመፅ በተባባሰባት ሀገር ስለሚደርሱ የመብት ጥሰቶች የሚመረምር ቡድንም ማደራጀት አስቧል። ከዚህም ሌላ የህብረቱ አላማ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ውይይት በዩጋንዳ አልያም የህብረቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ለመጥራት ነው። የብሩንዲ ፕሬዚዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን ምረጡኝ ማለት ከጀመሩበት ሚያዚያ ወር አንስቶ በሀገሪቱ ህዝባዊ አመፅ ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር ።በአመጹ ከ 100 በላይ ሰዎች ህይወትም ጠፍቷል።ንኩሩንዚዛ ያሸነፉበትን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የአውሮፓ ህብረትም ይሁን ዩናይትድ ስቴትስ እውቅና አልሰጡትም።
ልደት አበበ
ኂሩት መለሰ