1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ተጀመረ

ቅዳሜ፣ የካቲት 11 2015

የተባበሩት መንግሥታት ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬታማነት፣ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲኖር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገልፀዋል። አፍሪካ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈተነች መሆኗን በማስታወስ ለዘላቂነት ያለው ሰላም፣ ልማትና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲኖር አጋዥ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

Äthiopien | AU Gipfel in Addis Ababa
ምስል Solomon Muchie/DW

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ

This browser does not support the audio element.


ከ 51 ሀገሮች የተውጣጡ ልዑካን ቡድኖች እየተሳተፉበት ነው የተባለው 36 ኛው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ 35 ርእሰ ብሔሮች ፣ 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የህብረቱ አባል ያልሁኑ የስድስት ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ እና የአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናትም ታድመውታል።
ጉባኤው ዛሬ የካቲት 11 ሲጀመር ንግግር ካደረጉት መካከል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ" በሚለው የሕብረቱ መርህ ላይ ኢትዮጵያ ፀንታ ትቀጥላለች ብለዋል። አፍሪካውያን ልዩነቶቻቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው
ብሎም አፍሪካ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቢያንስ በአንድ ቋሚ መቀመጫ እንድትወከልም ጠይቀዋል።
አህጉሩ የበለፀጉት ሀገራት ስብስብ በሆኑት በ G 7 እና G 20 እንዲሁም በሌሎች አለምአቀፍ መድረኮችና ስብስቦች በአግባቡ እንድትወከልና የራሷን መልካም ገጽታ የምታስተጋባበት አለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እንዲኖራትም ጉባኤተኛውን ጠይቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬታማነት፣ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲኖር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ  መሆኑን የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገልፀዋል። አፍሪካ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈተነች መሆኗን በማስታወስ ለዘላቂነት ያለው ሰላም፣ ልማትና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲኖር አጋዥ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
"የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበረት መንግሥታት ግንኙነት እንደዚህ ጠንካራ ሆኖ አያውቅም። አፍሪካ ተግባር ትፈልጋለች። በቅድሚያ የኢኮኖሚ ተግባር ያስፈልጋታል። አፍሪካ በአቅም ደረጃ የበለፀገች ናት። ሆኖም በአለም አቀፍ ድጋፍ ላይ የበለፀገች አይደለችም። በአፍሪካ ላይ መዋእለ ንዋይን ፈሰስ በማድረግ ወደ ብልጽግና ለማደግ ገንዘብ ያስፈልጋል። ነገር ግን ታዲጊ ሀገራት በዚህ ረገድ በስፋት ተዘንግተዋል። በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጭምር ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል።የፀጥታው ምክር ቤት፣ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የሚመሩበት የብሪተን ውድ ስርዓት አፍሪካ ምንም ውክልና የሌላት ለመሆኑ ትክክለኛ ማሳያዎች ናቸው። የግጭት መሰረታዊ መነሻ ምክንያቶችን እና የጦርነት ሥር የሄኑ ችግሮችን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል።የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተፅእኖ እና ትኩረት ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር 
በወጣቶች እና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ ሰላም፣ ዘላቂ ልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራትና የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎችን አቀናጅቶ የሚሰራ አለም አቀፍ ሥልት መቅረፅ ይኖርብናል።
ዲሞክራሲያዊ እና ግልፅ የአሰራር ሥርዓቶች የሚጠናከሩበትን ሁኔታ ለማሳደግ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ቁርጠኞች ነን።"
የአረብ ሊግን የወከሉ ሰው የአረብ - አፍሪካ ግንኙነትን የማጠናከር ፍላጎት መኖሩን ገልፀዋል።
በጉባኤው መክፈቻ አለም የገጠማት ዘርፈ ብዙ ችግር ተንፀባርቋል። ጦርነት ፣ ወረርሽኝ፣ የምጣኔ ሀብት ድቀት ፣ የአየር ንብረት ችግር ያስከተለው ድርቅ እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን በጋራ እንግታ የሚሉ ሀሳቦች ተንፀባርቀዋል።
የአፍሪካ ሕብረት የአንድ አመት የሊቀመንበርነት ኃላፊነታቸውን ዛሬ ያስረከቡት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት በአህጉሩ እያደገ የመጣውን ሽብርተኝነት እና ኢ - ሕገ መንግስታዊ የመንግስት ለውጤችን አሳሳቢነትም ጠቅሰዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ውስጥ የሚስተዋለውን ሽብርተኝነትን ለመከላከል በገንዘብ እንዲያግዝም ጠይቀዋል። በአህጉሩ "የግጭት በር ተዘግቶ የሰላም በር እንዲከፈት" ጠይቀዋል።
የሕብረቱን የሊቀመንበርነት ኃላፊነት የተረከበችው የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ ከነፃ የንግድ ቀጣናው ትግበራ ባለፈ ለሰላምና መረጋጋት ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም እንደ አህጉር ራስን ለመቻል ከፊታችን ብዙ ሥራ ይጠብቀናል ብለዋል። 36 ሚሊዮን አፍሪካዊያን በተለያየ ምክንያት ቀያቸውን ጥለው የመሰደዳቸውን አሳሳቢነትም በአብነት ጠቅሰዋል።የአውሮጳ ህብረትና የአፍሪቃ ህብረት አዲስ አጋርነት ተስፋ
"የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን እንዳለብን ሆኖ ግን ይህ ውጥናችን እንዲሳካ ትኩረት ልናደርግባቸው የሚገቡ ሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ። ሰላም እና መረጋጋት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች የአፍሪካ ራስን በራስ የመቻል ጉዳዮች ናቸው። ለሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት መስጠት አለብን ፣ በተለይም እነዚህን ጉዳዮች በመከላከል እና በንግግር ለመፍታት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።
አህጉራችን ዛሬም ድረስ በርካታ የውስጥ ግጭቶችን እየተጋፈጠች ትገኛለች።"
ዛሬ በተጀመረው 36 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እስራኤል በፍልስጤም ላይ እያደረሰች ነው የተባለ ጭፍለቃ ፣ ዘረኝነትን ተቋማዊ የማድረግ አካሃድ፣ አገዛዝ ፣ የከፋፍለህ ግዛ መርህን ሕጋዊ የማድረግ እንቅስቃሴ እንዲሁም አለም አቀፍ የመብት ጥሰቶችን ለማስቆም የአፍሪካ ሕብረት እንዲያግዝ ተጠይቋል።
አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሁለቱ ወገኖች መፍትሔ አልባ ግጭት በሰላም እንዲፈታ ሕብረቱ ጥረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ምስል Solomon Muchie/DW
ምስል Solomon Muchie/DW
ምስል Solomon Muchie/DW

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW