1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአፍሪቃ ቀንድ ዉስብስብ ዉጥረት፣ የዉጪ ኃይላት ጣልቃ ገብነትና ሥጋቱ

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ ኅዳር 5 2018

አፋር ክልል ዉስጥ ተሰነዘረ የተባለዉ ጥቃትና ትግራይ ክልል ደረሰ የተባለዉ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ድብደባ ደግሞ የተፈራዉ ጦርነት ሊጀመር «የኃይል መፈታተሺያ» ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አጭሯል።ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ የሱፍ ያሲን እንደሚሉት ተቀናቃኝ ሐይላት የጀመሩት መፈታተሽና የገጠሙት የቃላት ጦርነት ዳግም ጦርነት የማይቀር አስመስሎታል

«እነዚያ የቀይ ባሕር ዳርቻ ሐገራት በጋራ ፀጥታ እናስከብራለን ሲሉ---ዓለም አቀፍ ድጋፍም አያጡም»
አቶ ዩሱፍ ያሲን ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ።«---የኢትዮጵያ የተለያዩ ኃይሎችና የኤርትራ የኃይል አሰላፍ ዉስብስብ ያለ ነዉ---»ምስል፦ privat

 

ሕዳር 2011 የኢትዮጵያዉያን ትልቅ ርዕሥ ከመንፈቅ በፊት የተደረገዉ የመሪ ለዉጥ የፈነጠቀዉ  የሠላም፣ የፍትሕ፣ የዴሞክራሲ ተስፋ ነበር።ብዙ አልቆየም በየአካባቢዉ የጎሳ፣ የግዛት ይገባኛልና የፖለቲካ ግጭቶች በተለይም ምዕራብ ኦሮሚያ ዉስጥ እንዳዲስ የተቀጣጠለዉ ዉጊያ ተስፋዉን ያጠወልገዉ ያዘ።
ሕዳር 2013 ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥአዲስ ጦርነት ተቀሰቀቀሰ።ከሁለት ዓመት በኋላ ሕዳር 2015 የአብዛኛዉ ኢትዮጵያ ርዕሥ የጦርነቱ መቆም፣ ጦርነቱን ያስቆመዉ ሥምምነት እንዴትነትና ገቢራዊነቱ ነበር።ኤርትራንም ያሳተፈዉ ጦርነት በስምምነት ማብቃቱና የሥምምነቱ ገቢራዊነት ተተንትኖ ሳያበቃ አማራ ክልል ሌላ ግጭት ተቀሰቀሰ።

ዘንድሮ ሕዳር ደግሞ የኢትዮጵያመንግሥትና ደጋፊዎቹ ባንድ በኩል፣ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፣ የኤርትራ መንግሥትና ተከታዮቻቸዉ በሌላ በኩል ሆነዉ የሚወራወሩት የጠብ ቃላት የሌላ ጦርነት ሥጋት አስከትሏል።

                            የኃይል መፈታተሽ ይሆን?

ባለፈዉ ሳምንት አፋር ክልል ዉስጥ ተሰነዘረ የተባለዉ ጥቃትና ትግራይ ክልል ደረሰ የተባለዉ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ድብደባ ደግሞ የተፈራዉ ጦርነት ሊጀመር «የኃይል መፈታተሺያ» ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አጭሯል።ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ የሱፍ ያሲን እንደሚሉት ተቀናቃኝ ሐይላት የጀመሩት መፈታተሽናየገጠሙት የቃላት ጦርነት ዳግም ጦርነት የማይቀር አስመስሎታል።ግን አቶ የሱፍ እንደሚሉት ጦርነቱን ማን ይጀምረዉ ይሆን? እንዴት? እና የት? የሚሉና ሌሎች ዉስብስብ ጥያቄዎች መልስ አላገኙም።

ቶ ዩሱፍ  እንደሚሉት ጦርነት ከተጫረ እንደ ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን የመሳሰሉ የአካባቢዉ መንግሥታት ተፋላሚ ኃይላትን መርዳታቸዉ አይቀርም።ከኢትዮጵያና ከኤርትራ አልፎ ለአፍሪቃ ቀድም ተጨማሪ  ጥፋት ያስከትላል።ይሁንና «ኢትዮጵያ ወደብ ማግኘት አለባት» በሚለዉ ሐሳብ ላይ «የማይስማማ የለም» ይላሉ አቶ ዩሱፍ ግን እንዴት? አቶ ዩሱፍ ያሲን ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዉናል።ተከታዩን ማገናኛ በመጫን እንድታደምጡን እንጋብዛችኋን።

ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW