1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃው ቀንድ ውጥረት

እሑድ፣ ጥቅምት 10 2017

የአፍሪቃው ቀን አካባቢ ከፖለቲካ እና ወታደራዊ ውጥረት እምብዛም ተላቅቆ አያውቅም። የአካባቢው ሃገራት የፖለቲካ አሰላለፍና ጎራም ቋሚ አይደለም፤ በየጊዜው ይለዋወጣል።

የአፍሪቃ ቀንድ
የኤርትራ እና የግብጽ መሪዎችምስል Egyptian President Office//APAimages/IMAGO

የአፍሪቃው ቀንድ ውጥረት

This browser does not support the audio element.

 

የአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ ከግጭት ጦርነት የተላቀቀባቸው ጊዜያት እጅግ ጥቂት ናቸው። ከእነዚህ ማኅበራዊ ቀውስን ከሚያስከትሉ ኩነቶች ፋታ ቢያገኝ የፖለቲካ ውጥረት ተለይቶት አያውቅም። አሁንም ይኸው አዙሪት ቀጥሎ ተጓዳኞች ተፈራርቀው በመቧደን በአፍሪቃው ቀንድ ሌላ የጦርነት ድባብ ውጥረቱ አይሏል። የአካባቢው ሃገራት በተደጋጋሚ ጦርነት ውስጥ ያለፉና ኤኮኖሚያቸው የደቀቀ፤ የምዕራቡን ዓለም እርጥባን ጠባቂዎች፤ በብድር ጫና ከጎበጡ ድሀ ሀገር ተርታ ናቸው። ሆኖም ዛሬም መከራ የጠገበው ሕዝባቸው የተረጋጋ የድህነት ሕይወቱን በሰላም እንዳይገፋ ሌላ ስጋት አንዣቦበታል። ባለፈው ሳምንት የኤርትራ፣ ሶማሊያ እና የግብጽ መሪዎች አስመራ ላይ ተሰባስበው  ይፋ እንዳደረጉት የአፍሪቃውን ቀንድ ጸጥታ ብሎም ሶማሊያን ከውስጥም ሆነ ከውጪ የሚደርስባትን ጥቃት በጋራ ለመከላከል ተስማምተዋል። መነሻው ኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊያ ተነጥላ ዓለም አቀፍ እውቅና ባታገኝም እራስ ገዝ መሆኗን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ያደረገው ስምምነት መሆኑ ሲገለጽ፤ የህዳሴ ግድብ ከዓባይ ውኃ ድርሻዬን ያጎድልብኛል በሚል የምትሞግተው ግብጽ ደግሞ አጋጣሚውን እንተጠቀመችበት የአፍሪቃው ቀንድና ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተንታኞች ይገልጻሉ። ዶቼ ቬለ ለዚህ ሳምንት የአፍሪቃው ቀንድ ውጥረት ወዴት ያመራል? ሲል ሦስት የፖለቲካ ተንታኞችን ጋብዞ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ፤  አቶ ዳያሞ ዳሌ፤ ቀድሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለገለገሉ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩ የፖለቲካ የአፍሪቃው ቀንድ እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ፤ እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሰይድ የአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝ በውይይቱ ተሳትፈዋል።

ሙሉውን ውይይቱ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW