የአፍሪቃ አገሮች 100 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት አቀዱ
እሑድ፣ ኅዳር 26 2008ማስታወቂያ
ዛሬ በፓሪስ የጸደቀው ‘አፍሪ 100’ የተሰኘው እቅድ በዓለም ባንክ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ይደገፋል። እቅዱን ጀርመንም በገንዘብ የምትደግፍ ሲሆን የግሉ ዘርፍ ደግሞ ተጨማሪ 545 ሚሊዮን ዶላር ያበረክታል ተብሏል። የሩዋንዳው የተፈጥሮ ሐብት ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ «መሬታችንን መልሶ ማልማት እድገት ደህንነት እና የሥራ እድል ይፈጥርልናል።» ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ ኬንያ፤ ላይቤሪያ፤ ማዳጋስካር፤ ማላዊ፤ ኒጀር፤ ርዋንዳ፤ ቶጎ እና ዩጋንዳ በእቅዱ የተካተቱ አገሮች ናቸው። እስካሁን የአፍሪቃ መንግስታት የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ የማልማት እና አሁን የሚገኙ የደን ይዞታዎችን የከባቢ አየር ለውጥን ለመቋቋምና የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ በሚያስችል መንገድ ለመጠበቅ የሚያስችሉ 13 ሃሳቦች በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ አቅርበዋል።
እሸቴ በቀለ
ልደት አበበ