የአፍሪቃ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሲኖደስ ጉባዔ ፍጻሜ
ሰኞ፣ ጥቅምት 16 2002ማስታወቂያ
በስብሰባው ከ244 የሚበልጡ ካቶሊካውያን ጳጳሳት፣ 33 የአብያተ-ክርስቲያን ሊቃውንትና 29 ታዛቢዎች መሳተፋቸውን ተኽለእግዚእ ገ/የሱስ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። የዩናይትድ እስቴትስ ፣ ላቲን አሜሪካ ፣ እስያ፣ ኦሺኒያና አውሮፓ ካቶሊካውያን ርክበ-ጳጳሳትም በዚያው በቫቲካን እንደተገኙ ለአፍሪቃውያኑ የሃይማኖት ተጋሪዎቻቸው፣ የትብብር መልእክታቸውን አሰምተዋል። የተደመደመው የአፍሪቃውያን ካቶሊካውያን ጳጳሳት የሲኖ ዶስ ጉባዔ ዓላማ ምን እንደነበረም ፣ ካቀረቡት አንድ ሃሳብ ጋር በማያያዝ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ሊቀ-ጳጳሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ተኽለዝጊ ገ/የሱስ
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ