የአፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶች ችሎት
ሰኞ፣ ነሐሴ 4 2001ማስታወቂያ
ይህ ፍርድ ቤት በአዉሮጳና በአሜሪካ በተመሳሳይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቅጣት ከተመሰረቱት ዓለም ዓቀፍ ችሎቶች ጋ ሲደመር ሶስተኛዉ መሆኑ ነዉ። ፍርድ ቤቱ በሚቀጥሉት ወራት ለመጀመሪያ ጊዜ ሰብዓዊ መብቶችን የደፈሩትን የአፍሪቃ ተጠያቂዎች ጉዳይ እንደሚመለከትም ተነግሯል። ሆኖም በክፍለ ዓለሙ የፍርድ ቤቱን ስራ እንቀበላለን ያሉ ሁለት አገራት ብቻ ናቸዉ፤ ቡርኪናፋሶና ማላዊ። የአፍሪቃዉን የሰብዓዊ መብት ችሎት በተመለከተ በርሊን ላይ የአራት ቀናት ስብሰባ ተካሂዷል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ሸዋዬ ለገሠ