1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እጥረት

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 29 2015

ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ጋር በተያያዘ በዓለም ዉራ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አህጉሩን የኤሌክትሪክ ችግር ለመቅረፍ በመሰረተልማት ላይ መስራት ያስፈልጋል። ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት 567 ሚሊዮን ህዝብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አይደለም።

Weltspiegel 10.06.2021 | Südafrika Soweto | Stromausfall
ምስል Siphiwe Sibeko/REUTERS

ከሰሃራ በታች 567 ሚሊዮን ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ አይደለም

This browser does not support the audio element.

ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ጋር በተያያዘ በዓለም ዉራ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አህጉሩን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለማስተካከል በኃይል አቅርቦት እና መሰረተልማት ላይ መስራት ያስፈልጋል። ከሰሃራ በታች ባሉ  የአፍሪቃ ሀገራት 567 ሚሊዮን ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈጽሞ የለዉም። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት በዓለማችን በጣም ጥቂት በኤሌክትሪክ አገልግሎት ያለበት ክልል ነው። ይህም ማለት በአህጉሩ ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ግማሽ የሚያህሉት በቤት ዉስጥ ኤሌትሪክን ተጠቅመዉ ሥራ ለመሥራት፣ ለማቀዝቀዝ ወይም ሞባይል ስልካቸውን ለመሙላት አልያም ማዳበርያ እንዲላክላቸዉ በስልክ መልክት ማስተላለፍ አይችሉም።   

"ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ አገሮች ወደኋላ መቅረት በጣም ያሳዝናል" ያሉት የቀድሞው የናይጄሪያ የኤነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቡባካር ሳምቦ፣ እንደ እስያና መካከለኛው ምስራቅ ያሉ ሌሎች አካባቢዎች ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እየተቃረቡ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።  ይሁንና ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት አብዛኛዉ ነዋሪ በገጠር ገና መሰረተ ልማት በደንብ ያልተስፋፋበት ቦታ መኖሩንም አልካዱም።  

የከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት የኤሌትሪክ ችግር ምስል DW

በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙት የኃይል ጉዳይ የኤኮኖሚ ባለሞያ ሉንጊል ሚሽል ፤ በአፍሪቃ ቅድምያ የምንሰጠዉ ነገር ሌሎች ነገር በመሆኑ ,ኤሌትሪክ መሰረተ ልማት አለመስፋፋቱን ተናግረዋል።

«ሁላችንም የምናውቀው ዓለም አቀፋዊ የኑሮ ውድነት አለ። አፍሪቃ ከዓለም ድሃ አካባቢዎች አንዱ በመሆኗ ሰዎች ለምግብ ቅድሚያ እንደሚሰጡ ወይም ለጤና እንክብካቤ ቅድሚያ እንደሚሰጡ መገመት ይቻላል። ምናልባትም ከኤሌትሪክ በፊት ፤ልጆቻቸው ትምህርት እንዲማሩ ይፈልጋሉ።  ታዲያ ይህ ሁሉ ወደ ኃይል ማለትም የኤሌትሪክ ድህነት ወደምትሉት ይመራል።»

ምንም እንኳ በርካታ የአፍሪቃ አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይላቸውን በማስፋፋት ላይ ቢሆኑም፣ ከሰሃራ በታች ካሉት የአፍሪቃ አገር የህዝብ ቁጥር እድገት ጋር እኩል የሚራመድ አይደለም። በዚህም ምክንያት በጎርጎረሳዉያኑ 2021 ዓ.ም እና በ2011 ዓ.ም  በአካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኙ ሰዎች በአጠቃላይ ቁጥር በግምት ተመሳሳይ ሆኖ መቆየቱን የዓለም ባንክ እና ሌሎች ተቋማት ባወጡት ጥናት ጠቁመዋል።  በምዕራብና በመካከለኛው አፍሪቃ የሕዝብ ቁጥር መጨመር በዚህ ዘመን ከታየዉ ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በመብለጡ ምክንያት አብዛኛው ሕዝብ በጨለማ እንዲዋጥ ምክንያት ሆኗል።   የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አለመኖር ትምህርት፣ የጤና ጥበቃ ወይም ሥራ ለማግኘት ትልቅ እንቅፋት ሆንዋል። የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) እንደገለጸው ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገሮች ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ግማሽ የሚያህሉት የኤሌክትሪክ ኃይል የላቸውም፤ በያዝነዉ የፈረንጆቹ 2023 ዓመት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ፤ በዩኔስኮ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከአምስት የጤና ተቋማት መካከል ሦስቱ የኤሌክትሪክ ኃይል የላቸውም።

የአፍሪቃ የኤሌትሪክ ችግር ምስል Akintunde Akinleye/REUTERS

የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት በብዙ የአፍሪቃ አገሮች ችግር ነዉ። ለምሳሌ ያህል ፣ በደቡብ አፍሪቃ ከሚገኙ 11 ሃገራት መካከል ባለፉት አሥር ዓመታት ከተስፋፋው የኃይል መቆራረጥ የተረፉት አንጎላና ቦትስዋ ብቻ ናቸዉ። በአፍሪቃ  በኢንዱስትሪ የበለፀገችው ደቡብ አፍሪቃ በዚህ ዓመት ብቻ በቀን እስከ አስር ሰዓት ያህል ኤሌትሪክ ይጠፋ ነበር። 

የአፍሪቃ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያቶች የትየሌሌ ናቸዉ። ከእነዚህም መካከል ከእርጀ መሠረተ ልማት መዋቅር እና የተዋጣለት የጉልበት ሥራ እጥረት አንስቶ ሥርዓት አልበኝነት፣ የኤሌክትሪክ ወጪን አለመክፈል አልፎ ተርፎም፤  በዉኃ ኃይል በሚተማመኑት አገሮች ድርቅ የሚያስከትለዉ ችግር ይገኙበታል።

የአፍሪቃን የኤሌትሪክ እጥረት ለማስተካከል ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እሙን ነዉ። ይሁን እና  አህጉሪቱ የኤልትሪክ ኃይል መሰረተ ልማትን ለመዘርጋት የግል ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሹን እምብዛም አትማርክም።

አዜብ ታደሰ / ኬት ዎከር

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW