ትኩረት በአፍሪቃ
ቅዳሜ፣ የካቲት 27 2013
ማስታወቂያ
አፍሪቃ የኮሮና ወረርሽኝ እየተስፋፋባቸው ካሉ አህጉሮች አንዷ ናት። እስካሁን በ 47 የአፍሪቃ ሀገሮች 3,7 ሚሊዮን ሰዎች በተህዋሲው መያዛቸውን እና 100 ሺ ገደማ የሚሆኑ ደግሞ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ህይወታቸው እንዳለፈ ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት። ያደጉት ሀገራት በሽታውን በክትባት ለማጥፋት የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ። የአፍሪቃ ሀገራት ግን ክትባቱን የማምረትም ይሁን በገበያ ተሻምቶ ለመግዛት ሀብት ስለሌላቸው ለህዝባቸው በቂ ክትባት የማቅረባቸው ሁኔታ ያጠያይቃል።
በሌላ በኩል በግብጽ እና በሱዳን መካከል የወዳጅነት ትብብሩ ተጠናክሯል። የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ ዛሬ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ሱዳን ካርቱም ተጉዘዋል። አል ሲሲ በሱዳን በሚኖራቸው ቆይታ በሁለቱ ሀገሮች ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ግንኙቶችን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኩራሉ ተብሏል።
ገበያው ንጉሴ
ልደት አበበ