የአፍሪቃ ጉባኤ በኔዘርላንድ
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2014
አፍሪቃ የአየር ለውጥ እያስከተላቸው ያሉትን ችግሮች ለመቋቋም የሚያደርገውን ጥረት ለመገምገምና እርዳታ ለመለገስ የተጠራው ያፍርካና ያውሮፕ መሪዎች ስብሰባ ትናንት በሮተርዳም ዓለማቀፍ የአየር ለወጥ መቋቋሚያ ወይም ግሎባል ሴንተር ፎር አዳፕቴሺን ማዕክል ተከሂዷል። ጉባኤው ባለፈው በብርታኒያ ግላስጎ በተካሄደው አለማቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ( ኮፕ 26) በተወሰነው መሰረት በሚቀጥለው የህዳር ወር በግብጽ ሻርም ኤል ሼይክ ከተማ ከሚክሂደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በፊት፤ በተለይ በእንዱስትሪ የበለጽጉት አገሮች ላእፍርካ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቁሚያ ፕርግርሞች ማስፈጸሚያ የገቡትን ቃል ተግባሪዊነት ለምገምገምና ተጨማሪ አስተዋጾዎችንም ለማፈላለግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። የዚህን ስብሰባ አስፈላጊነትና ጠቃሚነት የስብሰባው መሪና የአለማቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ፓትሪክ ቬርኩየን ሲገልጹ፤ “የዛሬው ስብሰባ ከሁለት ወር በኋላ በአፍርካ ሻርም ኤል ሼይክ ለሚካሄደው የአፍሪቃ ኮፕ 27 ጉባኤ ስኬት ወሳኝነት አለው፤ በማለት መልዕክቱም የዓለማቀፉ ማህበረሰብ አፍሪቃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት የሚጠበቀበትን እንዲይደርግ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ በዓለማችን የሙቀት መጠን መጨምር ምክኒያት የመጣ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህም በእንዱስትሪ የበልጽጉት አገሮች ወደ ካባቢ አየር በሚለቁት ከፍተኛ የክርቦን ልቀት መጠን ምክኒይት መሆኑ የታወቀ ነው። አፍሪቃ፤ ምንም እንኳ ለአየር ብክለቱና ሙቀት መጨመሩ ተጠያቂ ባይሆንም፤ ባለንዱስትሪዎቹ አገሮች በፈጠሩት የአየር ለውጥ ምክኒያት ግን ከፍተኛ ተጠቂና ሰለባም ነው ። በጉባኤው የስኔጋል፤ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክና፤ የጋና መሪዎች በካል እንዲሁም የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በቪዲዮ አማካይነት ተካፍለው መለዕክታቸውን አስተላለፈዋል። ዓለማቀፍ ድርጅቶችና የገንዘብ ተቋማት እንዲሁም የበርካታ አገሮች ሚኒስትሮችና የመሪዎች ተወካዮችም በስብሰባው ተገኝተዋል። ሆንም ግን በተለይ የአውሮጳ መሪዎች እዚህ ባቅራቢያቸው ባለችው የኒዘርላንድስ ከተማ ሮተርዳም በተጠራው ሰብሰብ አለመገኘታቸው በተለይ በአፍርካ መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል ። የወቅቱ የአፍርካ ህብረት ሊቀመንበር የሆኑት የሲኔጋል ፕሬዝዳንት ሚስተር ማኪ ሳል ይህን ቅሬታቸውን በግልጽ በማውጣት፤ “ እኛ እዚህ ድረስ መምጣት ከቻልን እነሱም ይችሉ ነበር በማለት የተስማቸውን ተናግረዋል ።
የመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ዋን ጸሀፊ ወይዘሮ አሚና መሀመድም የዓለማችንን የሙቀት መጠን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴሊሺየስ ዝቅ ለማድረግ የገባነውን ቃል ተግብራዊ ላማድረግ ጥረታችንን መቀጠል አለብን በማለት፤ በሰብሰብው የተገኙትን አመስግነው ያልተገኙት እንዲገኙና ግዴታቸውንም እንዲወጡ፤ ትግሉ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። “አራት የአፍርካ መሪዎች በሰብሰባው ተግኝተዋል። አስተናጋጇ አገር ነዘርላንድስም ይህን ስብሰባ እውን በማድረግ ተባብራለች። የአፍሪቃ ልማት ባንክ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የአለም የንግድ ድርጅትም ተግንተዋል። በእርግጥ ያልመጡት ያጎላሉ። እንዲመጡና ግዴታቸውንም እንዲወጡ ግን መታገል አለበን ብለዋል ለዲደብሊው በዚህ ጉዳይ በሰጡት አስተይየት።
የመዕራቡ አለም በተለይም አዉሮጳ፤ በዩክሬን ጦርነትና ኮቪድም ባስክትለው ችግር ምክኒያት የአየር ንብረት ለውጥ የመሳሰሉትን አለማቀፍ ጀንዳዎች ትኩረት እየሰጠው እንዳልሆነ እየተገለጸ ነው። በዚህም ምክኒያት በርካታዎቹ የአዉሮጳ መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚፓ ፕሮግራሞች መርጃ ገንዘብ፤ ለአፍርክ ለመስጠት የገቡትን ቃል መፈጸማቸውን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። ዲደብሊው የሰብሰባው ተባባሪ አዘጋጅና መሪ የሆኑትን ፕሮፊሰር ፓትሪክን አሁን በአለማችን ካለው ሁኒታ አንጻር መዕራባውያን በተለይም አውርፓ ቃልና ተግባር ለማዋሀድ መቻሉንም ጠይቆ ነበር፡ ‘በመጀመሪያ ድረጃ ሁላችንም አሁን በዙሪያችን ስላለው ሁኒታ የማንረዳ አይደለንም። በዩክሬን ያለውን ሁኒታና በምግብና በህየል ላይ ይተፈጠረውን የዋጋ ንረት እንረዳለን። ግን ደግሞ ሁላችንም ያየር ንብረት ለውጥ ሰሰባዎች በመሆናችን ያስክተለውን ችግርና ያንዣበበውን አደጋ ለመከላከል የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት ተስፋም ስጋትም እንዳላቸው አስታውቀዋል።
ስብሰባው በመጨረሻም አፍርካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክኒያት በክፍተኛ ችግር ላይ መሆኑንና አለምቀፉ ማህብረሰብ የሚጠበቀበትን ማድረግ ያለበት መሆኑን፤ በአየር ንብረት ለውጥ ዋናው ተጠቂ አፍሪክ መሆኑን ፤ በግላስኮው የአየር ንብረት ጉባኤ የተላለፈውን ውስኔ ተግባዊ ማድረግ ሞራዊ ግዴታ መሆኑን፤ እንዲሁም ፤ የዓፍርካን የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ፕርግራም መደገፍና መርዳት፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ግቦች መሳካት አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጹ ባለአምስት ነጥቦች መግለጫ በማውጣት በኒዘርላንድሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር ማርክ ሩተ የመዝጊያ ንግግር ጉባኤው ተጠናቋል
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ