1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰሞነኛ ኹነቶች

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 10 2017

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ ፕሬዚዳንት አሸማጋይነት ውዝግባቸውን በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ለቱርክ የዲፕሎማሲ ስኬት፣ ለአፍሪካ ሕብረት የውድቀቱ ማሳያ እንዲሁም ቱርክን በአባልነት አልቀበልም ላለው አውሮጳ ሕብረት ኪሳራ ነው ሲሉ አንድ የጅኦ ፖለቲካ ተንታኝ ገለፁ።

የአፍሪቃ ህብረት ስብሰባ  በአዲስ አበባ 17.02.2024
የአፍሪቃ ህብረት ስብሰባ በአዲስ አበባ 17.02.2024 ምስል Solomon Muchie/DW

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰሞነኛ ኹነቶች

This browser does not support the audio element.

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰሞነኛ ኹነቶች

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ ፕሬዚዳንት አሸማጋይነት ውዝግባቸውን በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ለቱርክ የዲፕሎማሲ ስኬት፣ ለአፍሪካ ሕብረት የውድቀቱ ማሳያ እንዲሁም ቱርክን በአባልነት አልቀበልም ላለው አውሮጳ ሕብረት ኪሳራ ነው ሲሉ አንድ የጅኦ ፖለቲካ ተንታኝ ገለፁ። በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል ሁሉን አቀፍ ወታደራዊ ስምምነትከተፈረመ ቆይቷል የሚሉት እኒሁ ተንታኝ ቱርክ በሶማሊያ ሮኬቶችን ለማስወንጨፍ የሚያስችል ተቋም እየገነባች ነው መባሉ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ካስማማች በኋላ የመጣ አዲስ ኹነት ሳይሆን የቆየው ወታደራዊ ስምምነት አካል ነው ብለዋል።

በሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተደረገው የመግበቢያ ስምምነት ከሞቅዲሾ እውቅና ውጪ የተደረገ ከመሆኑ የተነሳ እንዲሁም ሞቅዲሾም አብዝታ ስትቃወመው የቆየችው ጉዳይ ከመሆኑ አንፃር "ቀሪ ተደርጓል የሚል እንድምታ ይኖረዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

ለቱርክ ስኬትን፣ ለአፍሪካ ሕብረት ኪሳራን ያስከተለው ስምምነት

ስማቸውን ትተው ሀሳባቸውን ያጋሩን አንድ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ግለሰብ የባህል እና የሃይማኖት ስብጥር የሚስተዋልበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዘይትን ጨምሮ የተፈጥሮ ማዕድናት የሌሉት ሆኖ ሳለ ብዙ ዐይኖች የሚበዙበት ካለው ማህበራዊ መስተጋብር የተነሳ ብዙ መጠላለፎች የሚታዩበት በመሆኑ ነው ይላሉ። ለዚህም ነው የተለያዩ ሀገራት እጃቸውን የሚያስገቡበት በማለት አካባቢው ሃይማኖታዊ ጉዳዮች በፖለቲካ ሥሪቶች ውስጥ ታሳቢ የሚደረጉበት መሆኑም ሌላ አስረጂ አድርገው ይጠቅሳሉ።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን አሸማጋይነትየኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ግንኙነትበሰላም ለመፍታት የተደረሰው ስምምነት የዚህ የብዙ አካላት ፍላጎት አንዱ ማሳያ መሆኑን በመጠቆምም ሂደቱ አትራፊ እና ከሳሪ አካላትን በግልጽ የለየ ስለመሆኑም ይናገራሉ።

"የቱርክ የሶማሊያን እና የኢትዮጵያን መንግሥታት አደራድራ የአንካራ ስምምነት ማስፈፀሟ በዲፕሎማሲው ረገድ በርትታ እየወጣች ያለች፣ ተደማጭነቷ ከፍ እያለ የመጣ መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ለምዕራባዊያን የኪሳራ ምልክት ነው"። ብለዋል

የአንካራው ስምምነት ለአፍሪካ ሕብረት ምን ማለት ነው?

የአንካራው ስምምነት በዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቀባይነት ያላቸውን የባህር በር የማግኘት የሀገራት ሕጋዊ መብቶችን የያዙ መርሆዎችን እንደገና ያረጋገጠ ነው የሚሉት ተንታኙ አሳሪ ውል ነው ማለት ግን እንደማይቻልና እንደሚቸግራቸው ገልፀዋል። 

"ለአፍሪካ ሕብረት ትልቅ ዲፕሎማቱክ ኪሳራ ነው። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ እንሰጣለን ብሎ ለተነሳ ተቋም ጉዳየ ብሎ ሲወያይበት፣ መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ አላየንም" 

ቱርክ እና ሶማሊያ የቆየ ወታደራዊ ስምምነት አላቸው 

ዳመርጆግ ወደብ - ጅቡቲ ምስል Solomon Muchie/DW

በሌላ በኩል ቱርክ ከሶማሊያ ሮኬቶችን ለማስወንጨፍ የሚያስችል ተቋም እየገነባች ስለመሆኑ መረጃዎች ወጥተዋል። የጅኦ ፖለቲካ ተንታኙ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶኻን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የኦቶማን ቱርክን ገናና አገዛዝ የመመለስ ትልም ያለው መሆኑን በመጥቀስ ወታደራዊ ስምምነቱ ግን ቀደም ብሎ የተፈፀመ ነው ይላሉ።

"በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል ሁሉን አቀፍ ወታደራዊ ስምምነት ከተፈረመ ቆይቷል። የባህር በርን መጠበቅ፣ ማሰልጠን፣ ማስታጠቅ ወዘተ። ማዕድን መፈለግን የሚጨምር ሁሉ ከተፈረመ ቆይቷል። ምናልባት ሮኬትን ማስወንጨፍ የሚለው የሽምግልናው ውጤት ነው የሚል አረዳድ ይለኝም"።

የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ዕጣ ፋንታ

ሊጠናቀቅ ቀናቶች የቀሩት የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በቅርቡ ሰላማዊ የሥልጣን ርክክብ ያደረገችውን ራስ ገዝ ሶማሊላንድ የፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ከሞቃዲሾ የሄዱት የአሜሪካ አምባሳደር ሀገራቸው "ለወደፊትም ከጎናችሁ ናት" ሲሉ ለራስ ገዟ አስተዳደር በጎ ነገር ተናግረዋል። የጅኦ ፖለቲካ ተንታኙ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ያደረገችው የመግበቢያ ስምምነት አንድም ከሶማሊያ እውቅና ውጪ የተደረገ ከመሆኑ የተነሳ፣ በላላ ጎኑ ሞቅዲሾ አብዝታ ስትቃወመው የቆየች ጉዳይ ከመሆኑ አንፃር "ቀሪ ተደርጓል የሚል እንድምታ ይኖረዋ" ብለዋል፤ ምንም እንኳን ሶማሊላንዶች የሁለቱ ሀገራት ስምምነት "የተለየ ጉዳይ ነው" በማለት "ሂደቱ ይቀጥላል" የሚል እምነት እንዳላቸው ቢገልፁም።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW