1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባዔ በደቡብ አፍሪካ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2016

19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ መድረክ ከ40 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ350 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን በጋዜጠኝነት፣ ፈተናዎች እንዲሁም መውጫ መንገዶች ውይይቶች እየተካሄዱ፣ ጥናቶች እየቀረቡ፣ በጋዜጠኞች መካከል የልምድ ልውውጥ እየተካሄደ ይገኛል።

 19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ
19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግምስል፦ Million Haileselassie/DW

የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባዔ በየዓመቱ ጁሃንስበርግ የሚካሄድ አህጉራዊ የጋዜጠኞች፣ አጥኚዎች እንዲሁም የሚድያ ዘርፍ ምሁራን የሚሰባሰቡበት ነዉ።

This browser does not support the audio element.

19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባዔ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ መድረክ ከ40 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ350 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን በጋዜጠኝነት፣ ፈተናዎች እንዲሁም መውጫ መንገዶች ውይይቶች እየተካሄዱ፣ ጥናቶች እየቀረቡ፣ በጋዜጠኞች መካከል የልምድ ልውውጥ እየተካሄደ ይገኛል። 
የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባዔ በየዓመቱ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ የሚካሄድ አህጉራዊ የጋዜጠኞች፣ አጥኚዎች እንዲሁም የሚድያ ዘርፍ ምሁራን መድረክ ነው። የዘንድሮው 19ኛ የአፍሪካ ምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባዔ በዚህ ሳምንት  ሰኞ ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለ ሲሆን በዚሁ መድረክ ከ40 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ350 በላይ ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎች እንዲሁም 147 ጥናት አቅራቢዎች የታደሙበት ሆንዋል።

19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግምስል፦ Million Haileselassie/DW

በኢትዮጵያ እየደበዘዘ ነው የተባለው የሚዲያ ሚና እና ሙያዊነት

ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ሴኔጋል እንዲሁም ከኤስያ ሀገራት ጭምር የመጡ በተለይም በአፍሪካ ጉዳዮች ዙርያ የሚሰሩ ጋዜጠኞች የዘንድሮው ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ጠበቃዎች እንዲሁም አክቲቪስቶችም በመድረኩ ይገኛሉ።

በጉባዔዉ እንደተገለፀው የምርመራ ጋዜጠኝነት በአፍሪካ መተግበርና ማስፋፋት ተጠያቂነትና ዴሞክራሲ ወሳኝ የተባለ ሲሆን አሁንም እንቅፋት ሆነው የቀጡሉ ችግሮች ግን በስፋት እንደሚታዩ ተመልክቷል። በደቡብ አፍሪካው ዊትስ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት መምህሩ አንቶን ሀርበር ያቀረቡት ጥናት እንደሚለው፥ 60 በመቶ በአፍሪካ የሚገኙ ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ጋዜጠኞች የምርመራ ዘገባ ለማዘጋጀት በሚያደርጉት ጥረት ከመንግስት ጨምሮ ከተለያዩ አካላት ማስፈራራት ይደርሳቸዋል ብለዋል። 24 በመቶ ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ሁሌም ስጋት አላቸው ይላል ጥናቱ።

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት እና የኤርትራ የፕሪስ ነጻነት

በመድረኩ ጋዜጠኞች ልምድ ይቀያየራሉ፣ መረጃ ይለዋወጣሉ፣ ጥናቶች ይቀርባሉ፣ በዘገባዎች ዙርያ ግምገማ ይደረጋል፣ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች አጫጭር ስልጠና ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአፍሪካ ጋዜጠኞች መካከል ግንኙነት የመፍጠር አጋጣሚ ይመቻቻል። ዛሬ ማታ በሚኖር መርሐግብር ደግሞ በዓመቱ የተሰሩ የምርመራ ዘገባዎች ተመርጠው ሽልማት ይሰጣቸዋል። ኮንፈረንሱ እስከ ያዝነዉ ሳምንት ረቡዕ ድረስ የሚቀጥል የጋዜጠኞች መድረክ ነው።

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW