1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሕአዲግን በዓል ተገዶ ማክበር

Merga Yonas Bulaዓርብ፣ ግንቦት 19 2008

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር «ኢሕአዲግ» ስልጣን የያዘበትን 25ኛ ዓመት ለማክበር በየቦታዉ ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል። በየድግሱ ላይ የመንግስት ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰቡ አባላት እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ግን ግብዣዉ እንዴት ነብር?

Äthiopien vor der Wahl EPRDF Anhänger in Addis Abeba
ምስል Reuters/Tiksa Negeri

[No title]

This browser does not support the audio element.

የበዓሉ ቀን ነገ ቢሆንም የመንግስት ሰራተኞች፣ ተማርዎች እና የማህበረሰቡ አካል የሆኑት በየአከባብያቸዉ ለበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። የጥሪዉም ይዘት አንድ አንዱ ክብረ በዓሉ በዉይይት እንደምከበር ግን ሰራተኞቹ ሰዓቱን አከብሮ እንድሳተፉ ያትታል። አንዳንዱ ደግሞ በዚህ ክብረ በዓል ተሳታፊ ካልሆኑ <<አስተዳደራዊ ርምጃ>> እንደምወሰድባቸዉ ይደነግጋል። በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የወጡ ፅሁፎች እንደሚያስረዱት ሐኪሞች ሳይቀሩ ሥራቸዉን ትተዉ በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ታዘዋል።


አዲስ አበባ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ በሰማባ/ነቀርሳ ልዩ ህክምና የሚሰጥ፣ አንዱ ነዉ። በማህብራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተሰራጨ የጥሪ ደብዳቤ እንደሚያመለክተዉ የ25ኛ ዓመት ክብረ ባዓል <<በደማቅ ሁኔታ>> ለማክበር ረቡዕ ግንቦት 17፣ 2008 ዓ/ም የሆስፒታሉ ሰራተኞች በአክሱም ሆቴል እንዲገኙ ያትታል። ቀጥሎም ይህ ቀን እንደ ስራ ቀን ስለሚቆጠር ሁሉም ሰራተኛ 2:30 ተገኝቶ ፊርማ እንዲፈርሙ፣ <<ያልፈረመ ሰራተኛ ከሥራ እንደ ቀረ ተቆጥሮ አስተዳደራዊ እርምጃ>> እንደሚወሰድበት ያትታል።

በሆስፒታሉ በነርስ ሙያ ላይ የሚሰሩት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ የተለጠፈዉን የጥሪ ወረቀት እንድህ ያነቡታል፣ «ያ የተለጠፈዉ ነገር እዉነት ነዉ። እሱም ያዉ ስብሰባ ላይ ያልተሳተፈ እንደሚቀጣ እና ስብሰባዉ ላይ መሳተፍ ግዴታ እንደሆነ ነዉ የተናገሩት። በስብሰባዉ ላይ የተገለጠዉ ባለፉት 25 ዓመታት ለህዝብ እሄን እሄን አድረገናል የሚል ነበር አጀንዳዉ እንጅ ሌላ ነገር አልነበረም። ሰረተኞችም ከቀሩ የምደርስባቸዉ ችግር ስለምያዉቁ ኑ ከተባሉ መሄዴድ እንጅ ሌላ አማረጭ አልነበራቸዉም። ከቀሩ ያዉ እንዳስፈራሩን ርምጃ መዉሰዳቸዉ አይቀርም።»

ምስል Reuters/Tiksa Negeri


የሆስፒታሉ ሁሉም ሰራተኞች ከሄዱ ሕሙማንን ማን ያክመዋል ተብሎ ሲጠየቁ፣ የተወሰኑት እዛ ቀርተዉ እንደነበሩ፣ ግን በቂ ሰራተኛ እዛ ስላል ቀረ የሚፈለገዉን አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስቸግር የሆስፒታሉ ሰራተኛ ይናገራሉ።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ በአዲስ አባባ የመገናኛ ነዋሪ የሆኑት ክብረ ባዓሉ አይከበር ማለት ሳይሆን መለስ ብሎ የተደረጉ ወይም እየተረጉ ያሉት ሁኔታዎች፣ እንዲሁም ይህን ክብረ በዓል ለማክበር የሚወጣ ወጭ ማሰብ እንደሚኖርባቸዉ አስታያየታቸዉን ይሰጣሉ። ከቅርብ ግዜ ወድህ <<ልቅ>> የሆነ አከባበር እየመጣ ነዉ የሚሉት አስተያይት ሰጭ በዓሉን የማክበር ትርጉሙ ምንድነዉ ይላሉ?

ምስል picture alliance/dpa


የሆስፒታሉ ጉዳይ «ድራማ ነዉ» የሚሉት አስተያየት ሰጭ ገዥዉ ፓርት «በዓልን በግድ እናከብር» ማለቱ «ሞኝ እና ጅላጅል»መሆኑን ያሳያል ሲሉ ትችታቸዉን ሰንዝረዋል። ሌላኛዉ የደብረማርቆስ ዩንቭርስቲ ተማሪ የሆኑት በግደጅ ዉጡ ባንባልም ስብሰባ ላይ እንድንሳተፍ ጥሪ ደርሶናል ይላሉ።

በዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ድረ-ገፅ ላይ እሄን ጉዳይ በተመለከተ አወያይተን ነብር። አስተያየት ሰጭዎቹም በዓሉ አይከበር ሳይሆን አገሪቱ ያለችበት የኢኮኖሚ፣ ረሃብ እና የፖለትካ ቀዉስ ታሳቢ ተደርጎ ቢተዉም ጥሩ ነበር የሚሉ ነበሩ። ሌሎችም «ግንቦት 20 ኢህአዴግ ደርግን ጥሎ ደርግ የሆነበት ጊዜ ነው» ሲሉ ትችታቸዉን ሰንዝረዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሓመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW