1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን የአቶም መረሃ-ግብር የጊዜ ገደብ ይራዘም ይሆን?

እሑድ፣ ኅዳር 14 2007

የኢራንን የአቶም መረሃ-ግብርን በተመለከተ የጋራ ነጥብ ላይ እስካሁን አልተደረሰም። የኢራንን የአቶም መረሃ- ግብር በተመለከተ ቪየና ላይ በተደረገዉ ዉይይት በቂ ዉጤት ላይ ባለመደረሱ የቴህራን መንግስት የተጨማሪ የግዜ ገደብ እንዲሰጥ ጠይቋል።

Iran Atomgespräche 21.11.2014 Wien
ምስል Reuters/L. Foeger

በኢራን የአቶም መረሃ-ግብር ላይ ዛሬ ቪየና ላይ በቀጠለዉ ዉይይት ምንም ነጥብ ላይ ካልተደረሰ ነገ የሚጠናቀቀዉ የግዜ ገደብ መራዘም እንደሚኖርበት ኢራንን የሚወክሉት ባለስልጣናት ገልፀዋል። ለዉይይት የሚራዘመዉ ግዜ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደሚሆንም ተያይዞ ተገልፆአል። በተባበሩት መንግሥታት ድምፅን በድምፅ መሻር መብት ያላቸዉ አምስት ሃገራትና ጀርመን ከቴህራን መንግስት ጋር፤ የኢራን የአቶም መረሃ-ግብር ለኒኩልየር ማምረቻነት ሳይሆን ለሰላማዊ የኃይል ምንጭ ጥቅም ላይ እንዲዉል ለማድረግ ረዘም ላለ ግዜ ድርድር ላይ መሆናቸዉ ይታወቃል። ኢራን የአቶም መረሃ-ግብሯን እንድትቀንስ ማዕቀብ የሚያርፍባት ከሆነ፤ በኤኮኖሚዋ ላይ ከባድ ቀዉስ እንደሚከተል ተመልክቷል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW